ጌታ ፡ ቅደምልኝ (Gieta Qedemelegn) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ስብስብ
(Collection)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 2:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ
የአንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ (፪x)

ጌታን ፡ የሚያስቀድም ፡ በኑሮው ፡ በቤቱ
አቅፎ ፡ እንደ ፡ ደገፈው ፡ እንደ ፡ እናት ፡ አባቱ
ያ ፡ ነው ፡ የአምላክ ፡ ወዳጅ ፡ ክብሩን ፡ የማይፈልግ
በክፉ ፡ በደጉ ፡ ከቶ ፡ ማይበረግግ

አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ
የአንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ (፪x)

በትዕግሥት ፡ ጠብቁ ፡ አምላክ ፡ ይቅደም ፡ የሚል
እራሱን ፡ በውርደት ፡ ከመስቀሉ ፡ ሚጥል
ያ ፡ ነው ፡ ያምላክ ፡ ወዳጅ ፡ ምኞቱን ፡ ያሟላ
ለያዘው ፡ ቁም ፡ ነገር ፡ ከቶ ፡ የማይላላ

አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ
የአንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ (፪x)

ጌታ ፡ እንድቀድምልህ ፡ በኑሮው ፡ መከራ
በእምባው ፡ እየታጀበ ፡ ለመዝሙር ፡ ሲጠራ
ያ ፡ ነው ፡ የአምላክ ፡ ወዳጅ ፡ ክብሩን ፡ የሰቀለ
ያጋንንትን ፡ ሥልጣን ፡ በእምባው ፡ ያቃጠለ

አዝ፦ ጌታ ፡ ቅደምልኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ሁሉ
የአንተ ፡ ስለሆነ ፡ በመከራ ፡ ድሉ (፪x)