እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው (Endiet Dinq Amlak New) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


()

ስብስብ
(Collection)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 2:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

የደን ፡ ልማቱ ፡ የገደል ፡ ስርገቱ
የወንዝ ፡ እርዝመቱ ፡ የቀላይ ፡ ውበቱ
የቆንጆ ፡ ገጽታው ፡ የቦታ ፡ ከፍታው
የባሕር ፡ ጥልቀቱ ፡ የሜዳ ፡ ስፋቱ
እኛ ፡ ምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው
እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምንሰግድለት
የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት

የሽቶ ፡ መዓዛው ፡ የሙዚቃ ፡ ቃናው
የለምለም ፡ እርካታው ፡ የመዝናኛ ፡ ቦታው
የመፋቅር ፡ ወዙ ፡ የትዳር ፡ ማገዙ
የፍጥረት ፡ ድምቀቱ ፡ የሰማይ ፡ ርቀቱ
እኛ ፡ ምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው
እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምንሰግድለት
የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት

የአበቦች ፡ ፍካታ ፡ የወፎች ፡ ጫጫታ
የቀለም ፡ መዋሃድ ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ መዋደድ
የእምነት ፡ እርካታ ፡ ሰላምና ፡ ደስታ
የፅዮን ፡ ውበቱ ፡ የእውነት ፡ ጥራቱ
እኛ ፡ ምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው
እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምንሰግድለት
የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት

ጐህ ፡ ሲቀድ ፡ ማለዳ ፡ ጨለማ ፡ ሲከዳ
የፀሐዩ ፡ ሙቀት ፡ የከዋክብት ፡ ብዛት
የደመናት ፡ ክምር ፡ ንጹህ ፡ ተስማሚ ፡ አየር
ሁሉን ፡ በስርዓቱ ፡ መሪ ፡ ለፍጥረቱ
እኛ ፡ ምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው
እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ ምንሰግድለት
የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት