Dereje Kebede/Collection/Amlakie Eregnayie New
< Dereje Kebede | Collection
ክንድህ ይበርታ በጠላትህ በር
ሥራቸው ይፍረስ ይድቀቅ ይሰበር ሃሌሉያ
ስምህ ይለምልም ዙፋንህ ይጽና
ለባሪያህ በጐ ውለሃልና ሃሌሉያ
አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ውዳሴን ከአፌ አንተን ከልቤ
ከቶም አይጠፋ ብኖር ተርቤ ሃሌሉያ
የቅርብ ወዳጄ የጦር አዝማቼ
ከቶ አትለየኝ ብቆይ ታክቼ ሃሌሉያ
ብቆም ብቀመጥ ብሄድ ብተኛ
አምላኬ አንተ ነህ የእኔ ጓደኛ ሃሌሉያ
ጽልመት ቢመጣ የመከራ ጉም
አንተን ጠርቼ እኔ አላፈርኩኝ ሃሌሉያ
ሕመም ሞትህን ሥጋዬ ለብሶ
ይዋረድ ይለፍ ጽዋህን ቀምሶ ሃሌሉያ
የጻድቁን ሞት ነፍሴ ተጠምታ
ትጥገብ አትፈር ስምህን ጠርታ ሃሌሉያ