From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
1. የዕውቀት ፡ ራስ ፡ የጥበብ ፡ ጌታ
ምንም ፡ ቢፈተን ፡ የማይረታ
በሰው ፡ አእምሮ ፡ አይገመትም
ወርዱም ፡ ስፋቱም ፡ አይዘልቅም
አዝ፦ አመልካለሁ ፡ ይህንን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ
አመልካለሁ ፡ በማንም ፡ የማይረታ
አመልካለሁ ፡ ግንበኞች ፡ የናቁትን
አመልካለሁ ፡ የማዕዘን ፡ ዕራስን
2. ፍቅሩን ፡ አይቼ ፡ ቀምሸዋለሁ
ፍጹም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለሁ
በመከራዬ ፡ እርሱ ፡ እየገባ
ይጋፈጠዋል ፡ እንዳልረታ
አዝ፦ አመልካለሁ ፡ ይህንን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ
አመልካለሁ ፡ በማንም ፡ የማይረታ
አመልካለሁ ፡ ግንበኞች ፡ የናቁትን
አመልካለሁ ፡ የማዕዘን ፡ ዕራስን
3. ጥፋቴን ፡ ሁሉ ፡ በፍቅር ፡ እያየ
ያሳልፈኛል ፡ ልጄ ፡ እያለ
ከሁሉም ፡ በፊት ፡ ፍቅሩ ፡ ሰብሮኛል
በመስቀሉ ፡ ላይ ፡ ነፍሱን ፡ ሰጥቶኛል
አዝ፦ አመልካለሁ ፡ ይህንን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ
አመልካለሁ ፡ በማንም ፡ የማይረታ
አመልካለሁ ፡ ግንበኞች ፡ የናቁትን
አመልካለሁ ፡ የማዕዘን ፡ ዕራስን
4. ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝም
እንደርሱ ፡ የሚሆን ፡ ከቶ ፡ አላገኝም
የውስጥ ፡ ችግሬን ፡ ሳልነግረው ፡ ያውቃል
ለእኔ ፡ ሲከብደኝ ፡ ይሸከመዋል
አዝ፦ አመልካለሁ ፡ ይህንን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ
አመልካለሁ ፡ በማንም ፡ የማይረታ
አመልካለሁ ፡ ግንበኞች ፡ የናቁትን
አመልካለሁ ፡ የማዕዘን ፡ ዕራስን
|