From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ደረጀ ፡ ከበደ (Dereje Kebede)
|
|
|
|
፩ (1)
|
አልበም (1)
|
| ቁጥር (Track):
|
፪ (2)
|
| ርዝመት (Len.):
|
3:20
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች (Albums by Dereje Kebede)
|
|
|
ያለፈው ፡ በደሌን ፡ ተወው
ጌታዬ ፡ አደራ ፡ አታስታውሰው
እባክህ ፡ እድል ፡ ስጠኝና
ልጅህ ፡ አድርገኝ ፡ እንደገና (፪x)
በደሌ ፡ በዝቶ ፡ ባ'መጻዬ ፡ ታውሬያለሁ
እንደገና ፡ አውጣኝ ፡ በሃጥያቴ ፡ አለቅሳለሁ
የማልረባ ፡ ነኝ ፡ ኃይል ፡ የሌለኝ ፡ ብኩን ፡ ፍጡር
አንተን ፡ ሳይሆን ፡ ሟች ፡ ስጋዬን ፡ የማከብር
ያለፈው ፡ በደሌን ፡ ተወው
ጌታዬ ፡ አደራ ፡ አታስታውሰው
እባክህ ፡ እድል ፡ ስጠኝና
ልጅህ ፡ አድርገኝ ፡ እንደገና (፪x)
አዲስ ሰው ፡ አ'ርገኝ ፡ እንደ ፡ በረዶ ፡ የነጻ
ከታሰርኩበት ፡ ከስጋዬ ፡ አውጣኝ ፡ ነጻ
አትግፋኝ ፡ ጌታ ፡ በጥፋቴ ፡ አትመረር
ከተውከኝማ ፡ ወዴት ፡ አገር ፡ ሄጄ ልኖር
ያለፈው ፡ በደሌን ፡ ተወው
ጌታዬ ፡ አደራ ፡ አታስታውሰው
እባክህ ፡ እድል ፡ ስጠኝና
ልጅህ ፡ አድርገኝ ፡ እንደገና (፪x)
ከእኔ ፡ የሚያስደስት ፡ አትጠብቅ ፡ አታገኝም
ስግብግብ ፡ ስጋ ፡ ተሸክሜ ፡ ከቶ ፡ አልነጻም
ብቻ ፡ ጌታዬ ፡ ፀጋህ ፡ ለ'ኔ ፡ ምሶሶዬ
ደጋፊዬ ፡ ነው ፡ እንዳትነሳኝ ፡ ባ'መፃዬ
ያለፈው ፡ በደሌን ፡ ተወው
ጌታዬ ፡ አደራ ፡ አታስታውሰው
እባክህ ፡ እድል ፡ ስጠኝና
ልጅህ ፡ አድርገኝ ፡ እንደገና (፪x)
|