ቆሜ ፡ ብጠብቅህ ፡ እስከ ፡ መገለጥህ (Qomie Betebeqeh Eske Megeleteh) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(1)

አልበም
(Dereje 1)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

እኔም እንደ ዼጥሮስ እወድሃለሁ ብልህ
እክድህ ይሆናል ቃላት ምን ሊጠቅምህ
ቆሜ ብጠብቅ እስከ መገለጥህ
ያነው ምስክሬ እኔ እንደማፈቅርህ

በሰላሙ ጊዜ ሃሌሉያ ብዬ
የሱስዬ ብዬ ጌታዬ ወደድኩህ
ያን ጊዜ አይደለም እርግጠኛው መውደድ
ሳይታይ ብርታቴ በፈተና መንገድ

እኔም እንደ ዼጥሮስ እወድሃለሁ ብልህ
እክድህ ይሆናል ቃላት ምን ሊጠቅምህ
ቆሜ ብጠብቅ እስከ መገለጥህ
ያነው ምስክሬ እኔ እንደማፈቅርህ

በትካዜ ሳምንት ደስ በማይል ሰኣት
ፍቅሬን ያኔ መዝን በልቅሶዬ ጠዋት
እንግዲህ ጌታ ሆይ በአፌ አልደልልህም
ላንተ ግልፅ ናቸው ልቤም ኩላሊቴም

እኔም እንደ ዼጥሮስ እወድሃለሁ ብልህ
እክድህ ይሆናል ቃላት ምን ሊጠቅምህ
ቆሜ ብጠብቅ እስከ መገለጥህ
ያነው ምስክሬ እኔ እንደማፈቅርህ

ያኔ ስትገለጥ በክብር ታጅበህ
ችግሬን አልፌ ፀንቼ ስቆይህ
በሙሉ አንደበቴ ጌታ እወድሃለሁ
ብዬ ለመናገር በፊትህ እደፍራለሁ