ርዕስ (Title) -

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

link={{{Artist}}}/{{{Album}}}


(Volume)

አልበም
(Album)

ቁጥር (Track):

(Track)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የ{{{ዘማሪ}}} ፡ አልበሞች
(Albums by {{{Artist}}})

የደረጀ ከበደ መዝሙር
ካሴት 1
ምስጋና እልልታ
ጌታዬ አነባ ለኔ አለቀሰ
ሙትን ሊያድን ብሎ ደሙን አፈሰሰ
ኤሎሄ ኤሎሄ አለ ጮሀ ወዳባቱ
ሐሩር ቢወርድበት ቢበዛ ጭንቀቱ
              ምስጋና እልልታ ይገባዋል ለርሱ ለሃያሉ ጌታ
              ምስጋና እልልታ ይገባዋል ለርሱ ለሞተልን ጌታ

ከሰይጣን ተዋጋ በራብ ተፈተነ
እንዳልሆነ ሆነ በስደት ባከነ
ከግብፅ ቤተልሄም ከናዝሬት ይሁዳ
ጭንቅ ፍዳዉን አየ ለኔ ሲል ተጎዳ
                ምስጋና እልልታ ይገባዋል ለርሱ ለሞተልን ጌታ
                 ምስጋና እልልታ ይገባዋል ለርሱ ለሃያሉ ጌታ

ሄሮድስ ለሰይፍ አጨው ጲላጦስ ለሚስማር
መቼ ከቶ ደላው ሲኖር በዚች ምድር
በምኩራብ ተፈበት መስቀል አሳዘሉት
ቀራንዎ ሰቅለው ጎልጎታ ቀበሩት
               ምስጋና እልልታ ይገባዋል ለርሱ ለሞተልን ጌታ
               ምስጋና እልልታ ይገባዋል ለርሱ ለሃያሉ ጌታ

በዚህ ሁሉ ፍዳ የኖረውን ጌታ
ነፍሴ ታመስግነው በመዝሙር በዕልልታ
ምስጋና ከሆነ የዉለታህ ካሳ
መዝሙሬን ተቀበል ዉዳሴ ሙገሳ

             ምስጋና እልልታ ይገባዋል ለርሱ ለሞተልን ጌታ
             ምስጋና እልልታ ይገባዋል ለርሱ ለሃያሉ ጌታ

[[Category:]]