ጌታን ፡ አመልካለሁ (Gietan Amelkalehu) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(1)

አልበም
(1)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ጌታን አመልካለሁ /2/
ከሱ ጋር ለመኖር
ጉዞ ጀምሬአለሁ /2/

በጽዮን ሀገሬ አብሬው ለመኖር
ጉዞ ጀምሬአለሁ ወደ ቅድስት ሀገር
ወደ ቅድስት ሀገር
ተስፋን ተሞልቼ ከጌታ ልገናንኝ
ስንቄን ተሸክሜ በጎዳና ላይ ነኝ
በጎዳና ላይ ነኝ

ጌታን አመልካለሁ /2/
ከሱ ጋር ለመኖር
ጉዞ ጀምሬአለሁ /2/

አቀበት በዛብኝ ብዬ አልመለስም
በልቤ ካለችው ከጽዮን አልቀርም
ከጽዮን አልቀርም
በቀንም በሌትም እሷን እያለምኩኝ
በተስፋ እጓዛለሁ ርስቴን እንዳገኝ
እርስቴን እንዳገኝ

ጌታን አመልካለሁ /2/አመልካለሁ
ከሱ ጋር ለመኖር
ጉዞ ጀምሬአለሁ /2/

ጌታ የጠብቀኛል ቤቴን አስናድቶ
እግዳው ነኝና እጆቹን ዘርግቶ
እጆቹን ዘርግቶ
ልጁ ደስ እንዲልኝ ተጨንቆ ተጠቦ
ይጠባበቀኛል ጌታ እጁን ዘርግቶ
ጌታ እጁን ዘርግቶ

ጌታን አመልካለሁ /2/አመልካለሁ
ከሱ ጋር ለመኖር
ጉዞ ጀምሬአለሁ /2/

ጌታን አመልካለሁ /2/አመልካለሁ
ከሱ ጋር ለመኖር
ጉዞ ጀምሬአለሁ /2/