እሮጦ ፡ ሮጦ (Eroto Roto) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(1)

የለም ይል ጀመረ
(የለም ይል ጀመረ)

ዓ.ም. (Year): 1982
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 3:22
ጸሐፊ (Writer): ደረጀ ከበደ
(dereje kebede
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ሮጦ ሮጦ ሳይደርስ የልቡ
ለሞተ አዝናለሁ ሳይሞላ አሳቡ
አንተ ግን በሕይወት ሰምተሃል ቃሉን
ፍርድ ባንተ ነው ብትንቅ ማዳኑን

ወንድሜ ስማ ቁምነገር ምክሬን ላንተ የሚበጅ
ሳትሆን በአንቀልባ አቅም ሳያንስህ እንደ ሕጻን ልጅ
ሞት አጥልቶብህ መቃብር ውጦህ ትንፋሽህ ሳይቆም
ጌታን ተቀበል ዋስትና አድርገው ሳትጠፋ ከአለም
    
እድሜ ጤዛ ነው ረጋፊ አበባ ባለም ስትኖር
የጭንቅ የስቃይ ዘመነ ለቅሶ ዋይታና ሽብር
የእፎይታህ ናፍቆት የሰላም ፍቅር ካለ በል
ጌታን ተቀበል እርሱ ታማኝ ነው ሁሉን ሊሰጥህ

ሮጦ ሮጦ ሳይደርስ የልቡ
ለሞተ አዝናለሁ ሳይሞላ አሳቡ
አንተስ በሕይወት ሰምተሃል ቃሉን
ፍርድ ባንተ ነው ብትንቅ ማዳኑን

ሌላ ምን አለ የሚያስጨንቅህ ላንተ ያቃተህ
ሱስ ነው መዋተት ባሪያው አድርጎ አንተን የገዛህ
ዝሙት ነው ስካር ያስፈራህ ጓዴ ካንተ አይሎ
ጌታን አማክረው እርሱ ችሎታል ሕይወቱን ከፍሎ

ወንድሜ ስማ ቁምነገር ምክሬን ላንተ የሚበጅ
ሳትውል ብትቀበል አቅም ሳያንስህ እንደ ሕጻን ልጅ
ሞት አጥልቶብህ መቃብር ውጦህ ትንፋሽህ ሳይቆም
ጌታን ተቀበል ዋስትና አድርገው ሳትጠፋ ከአለም
     እድሜ ጤዛ ነው ረጋፊ አበባ ባለም ስትኖር
     የጭንቅ የስቃይ ዘመነ ለብሶ ዋይታና ሽብር
     የእፎይታህ ናፍቆት የሰላም ፍቅር ካለ በልብህ
     ጌታን ተቀበል እርሱ ታማኝ ነው ሁሉን ሊሰጥህ