እንደ ፡ ጳውሎስ ፡ አርገኝ (Ende Pawlos Aregegn) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(1)

አልበም
(Dereje 1)

ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:12
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

እንደ ጳውሎስ አርገኝ እንደ ሲላስ
ማመስገንን እንዳውቅ በመከራ ስጓዝ X2

ዻውሎስና ሲላስ ሳሉ በወህኒ ታስረው
የምስጋና መዝሙር ዘመሩልህ አብረው
ያንን መንፈስ በእኔ ውስጤ ጨምርልኝ
በርሃብ በእርዛቴ በአንተ ደስ ይበለኝ

እንደ ጳውሎስ አርገኝ እንደ ሲላስ
ማመስገንን እንዳውቅ በመከራ ስጓዝ X2

የጎደለኝ ቢኖር አለማመስገን ነው
በትንሽ ፈተና ብስጭትጭት እላለሁ
ስደትና እስራት ሲመጣ ግርፋት
ኧረ እንዴት ልሆን ነው ጌታ በዚህ ህይወት

እንደ ጳውሎስ አርገኝ እንደ ሲላስ
ማመስገንን እንዳውቅ በመከራ ስጓዝ X2

በቀኝ የጠበኩት ግራ ሲሆንብኝ
በሁሉም ተመስገን ማለትን አስተምረኝ
በእንግድነት ቤቴ ለምን ላሳዝንህ
ባይሳካም ኑሮ ጌታ ላመስግንህ

እንደ ጳውሎስ አርገኝ እንደ ሲላስ
ማመስገንን እንዳውቅ በመከራ ስጓዝ X2

ለስምህ ስጠላ ወዳጅም ሲርቀኝ
አፌን በምስጋና አንተ ክፈትልኝ
ይቅር ማጉረምረሜ በትልቅ ትንሹ
አጥራው ገለባዬን በእጅህ አለ መንሹ

እንደ ጳውሎስ አርገኝ እንደ ሲላስ
ማመስገንን እንዳውቅ በመከራ ስጓዝ X2