Dereje Kebede/Adagnie Yesus/Zor Beyie Sayew
አጭር ጊዜ አይደለም ለረጅም ዘመናት
በድካም በትግል ላያሌ ዓመታት
በመውደቅ መነሳት በውጊያ በጭንቀት
እንደማያልፍ የለም አለፈ ያ እሳት (፫x)
አዝ
ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን
አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን
ማመን ይሳነኛል ኃይል አገኘው
ለካስ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ
ሥሙን አከብራለሁ (፫)
መራራ አይታኘክ የመከራ እንጀራ
የብቸኝነት ቤት እኔው ከእኔ ጋራ
እንቅልፌን አጥቼ ብዙ ለሊት አልፏል
ዛሬ ግን ታሪክ ነው ተረት ነው ይወራል (፫x)
አዝ
ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን
አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን
ማመን ይሳነኛል ኃይል ከየት አገኘው
ለካስ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ
ሥሙን አከብራለሁ (፫)
የሕይወቴ ማብቂያ ዛሬ ነው ያልኩበት
ዓይኖቼን ጨፍኜ ሞትን ያሰብኩበት
ቀውጤው ሰዓት አልፎ ማየቴ ደንቆኛል
ለካስ ጌታ ወዶኝ እጅ እግሬን ጠብቋል (፫x)
አዝ
ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን
አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን
ማመን ይሳነኛል ኃይል ከየት አገኘው
ለካ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ
ሥሙን አከብራለሁ (፫x)
የአብርሃም አምላክ በክንፉ ሸሸገኝ
ለካስ መጐዳቴን ተጐሳቁዬ አየኝ
ያን ሁሉ ሻካራ ያን ሁሉ ጐርባጣ
ጌታ ብርታት ሆነኝ ችዬው እንድወጣ (፫x)
አዝ
ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን
አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን
ማመን ይሳነኛል ኃይል ከየት አገኘው
ለካስ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ
ሥሙን አከብራለሁ (፫)