ኢየሩሳሌም (Yerusalem) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አዳኜ ፡ ኢየሱስ
(Adagnie Yesus)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ ኢየሩሳሌም ፡ ቅድስቲት ፡ ከተማ
የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛ ፡ እንኳ
ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ እርዳታ (፪x)

የናፈቀኝ ፡ ዜማ ፡ የቅዱስ ፡ ዝማሬ (፪x)
አልቀርም ፡ ሳልዘምር ፡ ከጻድቃን ፡ አብሬ
ከበጉ ፡ ዙፋን ፡ ሥር ፡ ሳልዞር ፡ በደስታ (፪x)
አልቀርም ፡ ሳላይሽ ፡ አንቺ ፡ ቅዱስ ፡ ቦታ

ማቋረጫው ፡ መንገድ ፡ ሊጠልፈኝ ፡ ቢነሳ (፪x)
ሳላየው ፡ አልቀርም ፡ የይሁዳን ፡ አንበሳ
ብቻዬን ፡ ብቀርም ፡ መንገደኛው ፡ ሸሽቶ (፪x)
ሳላየው ፡ አልቀርም ፡ ኢየሱሴ ፡ መጥቶ

የመናኝ ፡ ተራራን ፡ መቧጠጥ ፡ ቢያቅተኝ (፪x)
የበረሃው ፡ ጉዞ ፡ ውኃ ፡ ጥም ፡ ቢጐዳኝ
የሚያረካው ፡ ጌታ ፡ ሲመጣ ፡ ከሰማይ (፪x)
ይረዳኛል ፡ በርግጥ ፡ ያቺን ፡ ቦታ ፡ እንዳይ

አዝ፦ ኢየሩሳሌም ፡ ቅድስቲት ፡ ከተማ
የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛ ፡ እንኳ
ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ እርዳታ (፪x)

ኢየሩሳሌም ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ኢየሩሳሌም ፡ አዲስ ፡ ሕይወት
በድል ፡ ዳግም ፡ የምናይሽ ፡ የምንወርስሽ ፡ መቼ ፡ ይሆን
አይቀር ፡ ቁርጥ ፡ ነው (፫x)
ማረፊያችን ፡ እፎይታችን ፡ ስንወርስሽ ፡ ነው (፪x)