ይቅርታን ፡ ለማድረግ (Yeqertan Lemadreg) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አዳኜ ፡ ኢየሱስ
(Adagnie Yesus)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ምሕረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እንዲሆን ፡ እሻለሁ
እኔ ፡ ግን ፡ በቀልን ፡ ወዳጅ ፡ አድርጌያለሁ
ነፍሴ ፡ ተጐሳቁላ ፡ ከቶም ፡ ሳያምርባት
ተኮንና ፡ እንዳትኖር ፡ ይቅርታን ፡ አስተምራት
ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ እምቢ ፡ እያለው
እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ
ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ

ወንድሜን ፡ ማቁሰሌ ፡ እጅግ ፡ ይረሣኛል
የተበደልኩትን ፡ መቁጠር ፡ ይጥመኛል
ምናለበት ፡ ዛሬ ፡ ልቤን ፡ ብትጠርበው?
መቀጥቀጫው ፡ ብረት ፡ መዶሻ ፡ በእጅህ ፡ ነው
ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ እምቢ ፡ እያለው(አልሆን ፡ እያለው)
እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ
ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ

እጄን ፡ ለአንተ ፡ ሰጠሁ ፡ አንተ ፡ እንድታስተምረኝ
ለውጠኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ! ይኸው ፡ በእግርህ ፡ ሥር ፡ ነኝ
የበደለኝን ፡ ሰው ፡ ይቅር ፡ ብዬ ፡ እንዳልፈው
በቀልን ፡ ሳላስብ ፡ በፍቅር ፡ እንዳቅፈው
ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ እምቢ ፡ እያለው(አልሆን ፡ እያለው)
እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ
ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ

ምሕረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እንዲሆን ፡ እሻለሁ
እኔ ፡ ግን ፡ በቀልን ፡ ወዳጅ ፡ አድርጌያለሁ
ነፍሴ ፡ ተጐሳቁላ ፡ ከቶም ፡ ሳያምርባት
ተኮንና ፡ እንዳትኖር ፡ ይቅርታን ፡ አስተምራት
ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ እምቢ ፡ እያለው(አልሆን ፡ እያለው)
እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ
ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ

ወንድሜን ፡ ማቁሰሌ ፡ እጅግ ፡ ይረሳኛል
የተበደልኩትን ፡ መቁጠር ፡ ይጥመኛል
ምናለበት ፡ ዛሬ ፡ ልቤን ፡ ብትጠርበው?
መቀጥቀጫው ፡ ብረት ፡ መዶሻ ፡ በእጅህ ፡ ነው
ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ እምቢ ፡ እያለው(አልሆን ፡ እያለው)
እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ
ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ ። ፬X