Dereje Kebede/Adagnie Yesus/Yemimeta
ዘማሪ ደረጀ ከበደ ዶ/ር ርዕስ የሚመጣ አልበም አዳኜ ኢኢየሱስ
የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ ተቀናቃኝ የለው ወይም ባላጋራ ፊት ለፊት የሚቆም ግጥሚያ ከርሱ ጋራ (፪x) በአህዛብ ፊት ሊቀርብ በድንቅ ይገለጣል ብንወድም ባንወድም ኢየሱስ ይነግሳል (፪x)
የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ (፪x)
ከእንግዲህ ለውርደት ለሞት አይሰጥም አንድ ጊዜ በመስቀል ፈጽሟል ሁሉንም (፪x) ያነ እዳ ሊከፍል ዛሬ ዳኛ ሆኖ ይመጣል ጌታችን በክብር ተክኖ (፪x)
የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ (፪x)
ከዘመናት በፊት ሁሉን ጥለው ያሉ ለርሱ የተገዙ ሞፈር ቀንበር ሳይሉ (፪x) በታላቅ እልልታ በሆታ በደስታ በአይናቸው ያዩታል የዘላለሙን ጌታ (፪x)
የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ (፪x)
ከደመናው መሃል ግርማው የሚያስፈራ በመላዕክት ታጅቦ ከአገልጋዮች ጋራ (፪x) የቅዱሳን አባት ስሙም አማኑኤል በከዋክብት ደምቆ አሜን ከተፍ ይላል (፪x)
የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ (፪x)