Dereje Kebede/Adagnie Yesus/Wetmedu Tesebere
ዘማሪ ደረጀ ከበደ
ርዕስ ወጥመዱ ተሰበረ
አልበም አዳኜ ኢየሱስ
አቤቱ የታለ ጠላታችን
በነነ ከዓይናችን
ከእጁ ተወሰደ መውጊያው ቀስቱ
የታመነበቱ
ወጥመዱ ተሰበረ ሆ
እኛም አመለጥን
ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x)
ጉድጓድ ተቆፍሮ ነበር ለእኛ
ቁልቁል እንድንገባ
እግዚአብሔር ግን ፈጥኖ ፊት ቀደመ
ዲያቢሎስ ሰጠመ
ወጥመዱ ተሰበረ ሆ
እኛም አመለጥን
ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x)
በቁጥቋጦ መሃል ጠላት ጠምዶ
ሊጥለን አሳዶ
ሌት ከቀን አደባ ዐይኑን ከፍቶ
መና ሊቀር ለፍቶ
ወጥመዱ ተሰበረ ሆ
እኛም አመለጥን
ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x)
በሰልፍ ያስጨነቀን ብናኝ ሆነ
ኃይሉ ተበተነ
እንዳረጀ አንበሳ ዝንብ ወረረው
ድንፋታው ተለየው።