በሃሩር አልፈናል (Beharur Alfenal) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(Dereje 6)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

በሃሩር አልፈናል ቁርም ገራርፎናል
ድጡ አንሸራቶን ወድቀን ተነስተናል
እግዚአብሔር ይመስገን ኢየሱስ አግዞናል
ሁሉን ድል አድርገናል

በብርዳማው ሃገር ውርጩ እንዳይገርፈን
የማያረጅ ሸማ ኢየሱስ አለበሰን

በሃሩር አልፈናል ቁርም ገራርፎናል
ድጡ አንሸራቶን ወድቀን ተነስተናል
እግዚአብሔር ይመስገን ኢየሱስ አግዞናል
ሁሉን ድል አድርገናል

ሰባት ጊዜ ወድቀን ሰባቴ አንስቶናል
በመራብ በመጥገብ ሁሉንም ቀምሰናል

በሃሩር አልፈናል ቁርም ገራርፎናል
ድጡ አንሸራቶን ወድቀን ተነስተናል
እግዚአብሔር ይመስገን ኢየሱስ አግዞናል
ሁሉን ድል አድርገናል

ታርዘን አይተናል ሌሊት ተጉዘናል
እንቅፋትም መትቶን ቁስል ጠዝጥዞናል

በሃሩር አልፈናል ቁርም ገራርፎናል
ድጡ አንሸራቶን ወድቀን ተነስተናል
እግዚአብሔር ይመስገን ኢየሱስ አግዞናል
ሁሉን ድል አድርገናል

ውርደትን ክብርን ነፍሳችን አውቃለች
በኢየሱስ ብዙ አይታ በእርሱ ላይ ቆማለች

በሃሩር አልፈናል ቁርም ገራርፎናል
ድጡ አንሸራቶን ወድቀን ተነስተናል
እግዚአብሔር ይመስገን ኢየሱስ አግዞናል
ሁሉን ድል አድርገናል


ታርዘን አይተናል ሌሊት ተጉዘናል
እንቅፋትም መትቶን ቁስል ጠዝጥዞናል

በሃሩር አልፈናል ቁርም ገራርፎናል
ድጡ አንሸራቶን ወድቀን ተነስተናል
እግዚአብሔር ይመስገን ኢየሱስ አግዞናል
ሁሉን ድል አድርገናል

ውዳችንን ይዘን እርሱን ተደግፈን
ምድረ በዳን ዘልቀን ወጣን ተሸጋግረን

በሃሩር አልፈናል ቁርም ገራርፎናል
ድጡ አንሸራቶን ወድቀን ተነስተናል
እግዚአብሔር ይመስገን ኢየሱስ አግዞናል
ሁሉን ድል አድርገናል