ዓይኔን ከሰው (Aynen Kesew) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(Dereje 5)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ግራ ቀኝም አልል በአይኖቼ
እወድቃለሁና ሰልችቼ
ለውድቀት ካልሆነ በስተቀር
ይቅርብኝ ከሰው ሁሉም ነገር

ዓይኔን ከሰው አንስቻለሁ
አንተኑ ብቻ እጣራለሁ
ድል እስክትሰጠኝ እጠብቃለሁ
ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው
አንተን ማግኘት ጥበብ ነው

ጌታ አለኝ ብያለሁኝና
በድፍረት ፎክሬያለሁና
ስጠራህ ከተፍ በል ረድኤቴ
ልኩራብህ እርዳኝ መድኅኒቴ

ዓይኔን ከሰው አንስቻለሁ
አንተኑ ብቻ እጣራለሁ
ድል እስክትሰጠኝ እጠብቃለሁ
ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው
አንተን ማግኘት ጥበብ ነው

በጎነት ከቶ የት ይገኛል
ትልቁ ትንሹን ረግጦታል
ፍቅርስ ከወዴት ይጋዛል
ሰው ሰውን በጥርሱ አላምጦታል

ዓይኔን ከሰው አንስቻለሁ
አንተኑ ብቻ እጣራለሁ
ድል እስክትሰጠኝ እጠብቃለሁ
ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው
አንተን ማግኘት ጥበብ ነው

ጎልጎታ አናተ ላይ ሞተሃል
ከጉድጏድ ሽቅብ አርገሃል
ቀና በል አይሃለሁ አንተን
ቸር ወዳጅ የሌለብህ እንከን

ዓይኔን ከሰው አንስቻለሁ
አንተኑ ብቻ እጣራለሁ
ድል እስክትሰጠኝ እጠብቃለሁ
ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው
አንተን ማግኘት ጥበብ ነው

ግባ በአዳራሹ በልቤ
አንተ ነህ መኩሪያዬ ጥጋቤ
መስቀልህ በፊቴ ተስሎ
አፀናኝ ከእንቅፋት ከልሎ

ዓይኔን ከሰው አንስቻለሁ
አንተኑ ብቻ እጣራለሁ
ድል እስክትሰጠኝ እጠብቃለሁ
ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው
አንተን ማግኘት ጥበብ ነው

አቤቱ የማትለዋወጥ
ደካማነቴን የማትገልጥ
አንተ ነህ ኢየሱስ የናዝሬቱ
ጥበብ ነው በአንተ መመካቱ