Dereje Kebede/Adagnie Yesus/Ahadu Elalehugn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አሃዱ እላለሁ በምስጋና
አፌን እክፍታለሁ በምስጋና
እርሱ ያሰበልኝ በለጠና
የእኔ ከንቱ ሆኖ ቀርቷልና

ወጥቼ ወርጄ ብዙ አስቤአለሁ አውጠንጥኛለሁ
ልቤ እሰክሚጨነቅ በስጋ ጉዞ ተክለፍልፌአለሁ
ኋላ ግን በየሱስ ተሰብስቤያለሁ /፪

ፈቃዱን አውቄ በምስጋና ቃል ስሙን ጠርቼ
እውነተኛ ድምፁን ከአንደበቱ ጠርቶኝ ስምቼ
እርሱን እጠብቃለሁ ሌላውን ትቼ /፪

በከንቱ ነበረ መደካከሜ ላይ ታች ማለቴ
ነገ ዛሬ እንዲሆን በምኞት ሩጫ እጅግ መትጋቴ
አሁን ግን ልቀበል ከላይ ካባቴ /፪

እንግዲህ ካገኘሁ አጋዥ ከአርያም ሐሳቤን ጠቅላይ
ደቂቃም አታልፍም አይኔን አንስቼ ወደላይ ሳላይ
ድል ይላክልኛል ከሩቅ ከሰማይ /፪