Dereje Kebede/Adagnie Yesus/Adagnie Yesus
- Numbered list item
ዘማሪ ደረጀ ከበደ
ርዕስ አዳኜ ኢየሱስ
አዳኜ ኢየሱስ ገናናው
የእጄን ሰንሰለት በጠሰው
ተመስገን ልበል ልቀኝለት
በእግሩ ሥር ልውደቅ
ልስገድለት ይህም አነሰበት
ነፍሴን አስጨንቋት የጠላቴ ጩኸት
አይኖቼን ባቀና ከላይ ስመለከት
ከመቅደሱ ሆኖ እምባዬን አበሰ
ያሰረኝን ገመድ ጌታ በጣጠሰ
አዝ
አዳኜ ኢየሱስ ገናናው
የሞት ቀንበር ከቦኝ ያመፅ ፈሳሽ ውጦኝ ሲኦል አፉን ከፍቶ ባጥንቴ አስቀርቶኝ ስሞታ ነገርኩኝ ላምላኬ ሳልሰለች እግዚአብሔር ተቆጣ ምድር ተናወጠች
አዝ አዳኜ ኢየሱስ
ጠላቴን ሰበረ እንዳያንሰራራ ከቁጣው ጢስ ወጣ ፍምም ከሱ በራ ባእድ የረገጠኝ እንደመንገድ ጭቃ ነፃነቴን ሰጠኝ መቆዘሜ አበቃ
አዝ አዳኜ ኢየሱስ
ዛሬማ ሰው ሆኜ ቀስት እገትራለሁ በኮረብታ ቆሜ ምሥጋና እሰዋለሁ ፅኑ እግር ለሰጠኝ የማይንሸራተት ለናዝሬቱ ኢየሱስ እጥፍ ልስገድለት
አዝ
አዳኜ ኢየሱስ ገናናው