የጸና ፡ ግንብ (Yetsena Ginb) - ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ
(Dawit Wolde)

Dawit Wolde 1.jpeg


(1)

መዝሙር ፺ ፩
(Mezmur 91)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Wolde)

የጸና ፡ ግንብ ፡ ነው ፡ ያንተ ፡ ሥም ፡ ጌታዬ
በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ሆነኝ ፡ መጠጊያዬ
ጻድቅ ፡ ሥምህን ፡ ጠርቶ ፡ ከጉዳት ፡ ያመልጣል
ካስፈሪው ፡ ጨለማ ፡ ከጉድጓድ ፡ ይወጣል

አዝ:- ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ
ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ፡ መድኃኒቴ (፪x)

ሥምህ ፡ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ አምላኬ
ፈጥነህ ፡ ትደርሳለህ ፡ ስጮህ ፡ ተንበርክኬ
ከጨካኙ ፡ አውሬ ፡ ከሞት ፡ ኃይል ፡ ያድናል
የሥምህ ፡ ጉልበቱ ፡ ጠላቴን ፡ ይጥላል

አዝ:- ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ
ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ፡ መድኃኒቴ (፪x)

ብዙዎች ፡ ተነሱ ፡ በኃይል ፡ የገነኑ
ዝናቸው ፡ የናኘ ፡ ላፍታ ፡ ለሰሞኑ
ዝንታለም ፡ አልቆዩም ፡ እንደጥላ ፡ አልፈዋል
የኔ ፡ ጌታዬ ፡ ሥም ፡ ዛሬም ፡ ድንቅ ፡ ይሰራል

አዝ:- ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ
ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ

ወደ ፡ ኃይሉ ፡ ችሎት ፡ ገባሁ ፡ ያለከልካይ
አጋፋሪ ፡ አልቆመ ፡ ዘበኛ ፡ ደጁ ፡ ላይ
በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ በየትኛውም ፡ ቦታ
ፊቱ ፡ አፈሳለሁ ፡ የእንባዬን ፡ ጠብታ

የልቤን ፡ ብሶት ፡ ያያል ፡ ጩኸቴንም ፡ ያዳምጣል
እንባዬን ፡ ያብስልኛል ፡ እንደንስር ፡ ያድሰኛል

የጸና ፡ ግንብ ፡ ነው ፡ ያንተ ፡ ስም ፡ ጌታዬ
በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ሆነኝ ፡ መጠጊያዬ
ጻድቅ ፡ ስምህን ፡ ጠርቶ ፡ ከጉዳት ፡ ያመልጣል
ካስፈሪው ፡ ጨለማ ፡ ከጉድጓድ ፡ ይወጣል

አዝ:- ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ
ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ፡ መድኃኒቴ (፪x)

ሥምህን ፡ ሳነሳሳ ፡ ሰይጣን ፡ ይሸበራል
ባንድ ፡ መንገድ ፡ መጥቶ ፡ በብዙ ፡ ይሸሻል
በተኩላና ፡ በእባቡ ፡ ላይ ፡ እጫማለሁ
አንበሳ ፡ ዘንዶውን ፡ እረጋግጣለሁ

በጌታ ፡ እታመናለሁ ፡ ሥሙንም ፡ አውቀዋለሁ
ስጠራው ፡ ይመልስልኛል ፡ ማዳኑንም ፡ ያሳየኛል ፡ ያከብረኛል (፪x)