ይህ ፡ ለኔ ፡ ክብር ፡ ነው (Yih Lenie Kibir New) - ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ
(Dawit Wolde)

Dawit Wolde 1.jpeg


(1)

መዝሙር ፺ ፩
(Mezmur 91)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Wolde)

 
አዝ፦ የሰማይ ፡ የምድር ፡ የፍጥረት ፡ ንጉሥ
ለእኔ ፡ ይህ ፡ ክብር ፡ ነው ፡ አንተን ፡ ማወደስ
የቁጣ ፡ ልጅ ፡ ሳለሁ ፡ ቀድሞ ፡ ከፍጥረቴ
ሳስብ ፡ ይደንቀኛል ፡ በስምህ ፡ መጠራቴ
ተደምስሶ ፡ ኃጢአቴ ፡ የዕዳ ፡ ጽህፈቴ ፡ በአንተ ፡ በመታየቴ

ስምህን ፡ አነግሣለሁ ፡ ማዳንህን ፡ ስላየሁ
መዝሙር ፡ እዘምራለሁ ፡ ፍቅርህን ፡ ስላየሁ
እጥፍ ፡ አሰግዳለሁ ፡ ለክቡርነትህ
አምልኮ ፡ አቀርባለሁ ፡ ለአምላክነትህ

አዝ፦ የሰማይ ፡ የምድር ፡ የፍጥረት ፡ ንጉሥ
ለእኔ ፡ ይሄ ፡ ክብር ፡ ነው
አንተን ፡ ማወደስ ፡ አንተን ፡ ማሞገስ
ዝናህን ፡ ሰምቼ ፡ በዓይኖቼ ፡ አይቼ
ለክብርህ ፡ ሰገድኩኝ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ አልኩህ

ቤቱን ፡ የሞሉትን ፡ ፈሪሳውያንን ፡ ሳትፈራ
የናርዶስን፡ ሽቶ ፡ በእግሮቹ ፡ ሥር ፡ ሰብራ
እንባዋን ፡ አፍስሳ ፡ ክብሯን ፡ ሁሉ ፡ ጥላ
እንዳመለከችው ፡ የነፍሷን ፡ ከለላ
እኔም ፡ ከሕይወቴ ፡ ሳልቆጥብ ፡ ከአንጀቴ ፡ ዜማ ፡ መስዋዕቴ

አዝ፦ የሰማይ ፡ የምድር ፡ የፍጥረት ፡ ንጉሥ
ለእኔ ፡ ይሄ ፡ ክብር ፡ ነው
አንተን ፡ ማወደስ ፡ አንተን ፡ ማሞገስ
ዝናህን ፡ ሰምቼ ፡ በዓይኖቼ ፡ አይቼ
ለክብርህ ፡ ሰገድኩኝ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ አልኩህ

ገና ፡ በሩቅ ፡ ሳለሁ ፡ በስሜ ፡ ያወቅከኝ
የርስትህ ፡ ተካፋይ ፡ ወራሽ ፡ ያደረከኝ
ለሰው ፡ አስቸጋሪ ፡ ድካም ፡ ጉድለቴን ፡ ችለህ
ስወድቅ ፡ ስነሳ ፡ አይዞህ ፡ ልጄ ፡ ብለህ
በክንድህ ፡ ደግፈህ ፡ በፍቅር ፡ እጅህ ፡ ዳሰህ
አቆምቀኝ ፡ ሰው ፡ አርገህ

ሥምህን ፡ አነግሳለሁ ፡ ማዳንን ፡ ስላየሁ
መዝሙር ፡ እዘምራለሁ ፡ ፍቅርህን ፡ ስላየሁ
እጥፍ ፡ አሰግዳለሁ ፡ ለክቡርነትህ
አምልኮ ፡ አቀርባለሁ ፡ ለአምላክነትህ

አዝ፦ የሰማይ ፡ የምድር ፡ የፍጥረት ፡ ንጉሥ
ለእኔ ፡ ይሄ ፡ ክብር ፡ ነው
አንተን ፡ ማወደስ ፡ አንተን ፡ ማሞገስ
ዝናህን ፡ ሰምቼ ፡ በዓይኖቼ ፡ አይቼ
ለክብርህ ፡ ሰገድኩኝ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ አልኩህ
ጌታ ፡ አምላኬ ፡ አልኩህ (፬x)