ፈገግታ (Smile) - ዳዊት ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ ወልዴ
(Dawit Wolde)


(1)

መዝሙር ፺ ፩
(Mezmur 91)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Wolde)

የትም ፡ ባክኜ ፡ እንዳልጠፋ ፡ እንደሌላቸው ፡ ተስፋ
አምላኬ ፡ ጐዳናዬን ፡ መንገዴን ፡ አሰፋ
ደረቁን ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ በውሃ ፡ እንዲረካ
በምንጩ ፡ ደስ ፡ አሰኘኝ ፡ ጨለማዬ ፡ ፈካ
የመርገም ፡ ጨርቄን ፡ ቀደደዉ ፡ መተላለፌን ፡ አራቀዉ
እግሬን ፡ አጸና ፡ በከፍታ ፡ ወዶ ፡ አዳነኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ

በተከበበች ፡ ከተማ ፡ አጽናኝ ፡ ድምጽ ፡ እያሰማ
በአስደናቂ ፡ ምሕረቱ ፡ አኖረኝ ፡ በቤቱ
ሲጠብቀኝ ፡ መች ፡ ሰንፎ ፡ አቤት ፡ ስንቱን ፡ አሳልፎ
ከቶ ፡ አለ ፡ ለታምራቱ ፡ ከልቤ ፡ ተጽፎ

በባዕድ ፡ ምድር ፡ ጓደኛዬ ፡ (ጓደኛዬ)
ሳዝን ፡ መጽናኛዬ ፡ (መጽናኛዬ)
ታሪኬን ፡ ሞላው ፡ በመዝገቡ
ከፍ ፡ ይበልልኝ ፡ ታላቅ ፡ ስሙ

አፌን ፡ ሞላው ፡ በሳቅ ፡ ዝማሬ ፡ ተረጋጋ ፡ ዙሪያ ፡ ሰፈሬ
ስለ ፡ ሥሙ ፡ ያደረገው ፡ ምስጋናው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)

ጌታ ፡ ፊት ፡ አይቶ ፡ አያዳላ ፡ አምላኬ ፡ የምስኪን ፡ ጥላ
ተማምነው ፡ ለጠበቁት ፡ ይደርሳል ፡ ሲጠሩት
እኔም ፡ እርሱን ፡ ታምኜ ፡ በእድሜ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ
አልቀረሁም ፡ በከንቱ ፡ አለሁኝ ፡ በቤቱ

አባ ፡ አባት ፡ ብዬ ፡ ተጣርቼ ፡ (ሥሙን ፡ ጠርቼ)
በእምባ ፡ በጸሎት ፡ ደጅ ፡ ጠንቼ
ምልጃዬን ፡ ሰምቶ ፡ (ምልጃዬን ፡ ሰምቶ) ፡ አልጨከነም
(ምሕረቱን ፡ ከእኔ) ፡ ምሕረቱን ፡ ከእኔ ፡ አላራቀም

አፌን ፡ ሞላው ፡ በሳቅ ፡ ዝማሬ ፡ ተረጋጋ ፡ ዙሪያ ፡ ሰፈሬ
ስለ ፡ ሥሙ ፡ ያደረገው ፡ ምስጋናው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፯x)

ምስጋናው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ (፫x)