መዝጊያ (Outro) - ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ
(Dawit Wolde)

Dawit Wolde 1.jpeg


(1)

መዝሙር ፺ ፩
(Mezmur 91)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Wolde)

አዝ:- አንተን ፡ ጠርቶ ፡ ማን ፡ አፈረ
ተማምኖብህ ፡ ማን ፡ ከሰረ
የተዘጋን ፡ ትከፍታለህ
የታሰረን ፡ ትፈታለህ
የታመመን ፡ ታድናለህ
የሞተውን ፡ ታስነሳለህ
ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ጌታዬ ፡ ሆት ፡ ስልጣን ፡ የአንተ
ስልጣን ፡ የአንተ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ስልጣን ፡ የአንተ
ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ስልጣን ፡ የአንተ

የፈጠረን ፡ በረሃ ፡ በሌለበት ፡ ውሃ
በምድረበዳ ፡ ለተጐዳ
ዘመድ ፡ ለሆነው ፡ ባዳ ፡ እንደ ፡ ማለዳ
አምቆ ፡ ሚስጥሩን ፡ በልቡ ፡ ጓዳ
እንባውን ፡ የጻፈ ፡ በጸሎት ፡ ሰሌዳ
ለቆዘመው ፡ ብቸኛ ፡ ለሌለው ፡ ጓደኛ
ሃሩር ፡ ላከሰለው ፡ ፡ መንገደኛ
የሚቀምሰው ፡ ላጣ ፡ ረሃብተኛ
በሀገር ፡ በምድሩ ፡ ስደተኛ
በወገኑ ፡ መሃል ፡ መጻተኛ
ድሃ ፡ ችግረኛ ፡ የሆነም ፡ እንደኛ
ለሚሻህ ፡ ቅን ፡ ፈራጅ ፡ ዳኛ
ከቤቱ ፡ ሳይወጣ ፡ መናን ፡ የሚሻ
ለነፍሱ ፡ አጽናኝ ፡ ደራሽ ፡ አዛኝ ፡ ለስብራቱ ፡ ጠጋኝ
በሩን ፡ ዘግቶ ፡ ለሚያለቅሰው
ነገር ፡ ከብዶት ፡ ሆድ ፡ ለባሰው
አጥቶ ፡ እንባውን ፡ የሚያብሰው
ረድኤት ፡ የሚሆነው ፡ ከሰው
ማነው ፡ የሚደርሰው

ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፭x)

ለብቸና ፡ ተጓዥ ፡ መንገደኛ
የፍቅር ፡ አምላክ ፡ እውነተኛ
ፍቅር ፡ ማነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ፍቅር ፡ ማነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ኃጢአት ፡ አሸፍቶት ፡ ጫካ ፡ የገባውን
ጸጋውን ፡ ተገፎ ፡ የተራቆተውን
የበደሉን ፡ ብዛት ፡ መሸከም ፡ ላቃተው
ነገር ፡ ግራ ፡ ገብቶት ፡ ለሚወተውተው
የእዬዬ ፡ ኑሮ ፡ የለቅሶ ፡ ሸለቆ
የጨከነ ፡ ውጋት ፡ ሃዘናትን ፡ ዘልቆ
በጦርነት ፡ ሜዳ ፡ ፍልሚያ ፡ መሃል ፡ ወድቆ
ፈገግታ ፡ ከፊቱ ፡ ከቤቱ ፡ ሳቅ ፡ ርቆ
እንባው ፡ ካይኑ ፡ ደርቆ
ሃዘን ፡ ኑሮ ፡ ሲከፋ
ረዳት ፡ ወገን ፡ ሲጠፋ
ወጀብ ፡ አውሎ ፡ ሲከፋ
የመከራ ፡ ጉም ፡ ሲያካፋ
መስቀሉ ፡ ስር ፡ ሲደፋ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ደርሶ ፡ እንባውን ፡ አብሶ
የጽድቅ ፡ ልብስ ፡ አልብሶ ፡ አሮጌን ፡ አድሶ
በፍቅሩ ፡ እጁ ፡ ዳሶ ፡ በደሌን ፡ ደምስሶ
አጥቦና ፡ ቀድሶ ፡ ፈውሶ
በክብር ፡ ያቆማል ፡ ጥያቄን ፡ መልሶ

ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፭x)

አዝ:- አንተን ፡ ጠርቶ ፡ ማን ፡ አፈረ
ተማምኖብህ ፡ ማን ፡ ከሰረ
የተዘጋን ፡ ትከፍታለህ
የታሰረን ፡ ትፈታለህ
የታመመን ፡ ታድናለህ
የሞተውን ፡ ታስነሳለህ
ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ጌታዬ ፡ ሆት ፡ ስልጣን ፡ የአንተ
ስልጣን ፡ የአንተ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ስልጣን ፡ የአንተ
ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ስልጣን ፡ የአንተ