From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
"መዝሙር ፡ ፺፩"
“በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር
ሁሉንም ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል
እግዚአብሔርን ፡ አንተ ፡ መታመኝያዬ ፡ ነህ ፡ እለዋለሁ
አምላኬና ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ "
"መዝሙር ፡ ፺፩"
በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር
ሁሉንም ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል
እግዚአብሔርን ፡ አንተ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ እለዋለሁ
አምላኬና ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ (፪x)
አዝ:- ነፍሴን ፡ ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ከአደገኛው ፡ መንገድ
ከለሊቱ ፡ ግርማ ፡ ካስፈሪው ፡ ጨለማ
በቀን ፡ ከሚበረው ፡ ከጠላት ፡ ፍላጻ
በክንፎቹ ፡ ጋርዶ ፡ ሸሽጎኛልና
በእርሱ ፡ እታመናለሁ ፡ ያስጥለኛል
ስሙን ፡ አውቀዋለሁ ፡ ይጋርደኛል
በመከራዬ ፡ ጊዜ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
ታማኙን ፡ አምላኬን ፡ ላመስግነው
ላመስግነው ፡ ላመስግነው ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፬x)
አንዳንዴ ፡ እምነቴ ፡ ሲፈተንና ፡ ስታገል
አቋራጭ ፡ መንገድ ፡ ስፈልግ ፡ ቶሎ ፡ ልገላገል
ያን ፡ ጊዜ ፡ ይመጣና ፡ ቅዱስ ፡ ቃሉ ፡ ወደልቤ
ፈጥኖ ፡ ይመልሰኛል ፡ ካልተቀደሰው ፡ ሃሳቤ
አዝ:- ፡ ነፍሴን ፡ ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ከአደገኛው ፡ መንገድ
ከለሊቱ ፡ ግርማ ፡ ካስፈሪው ፡ ጨለማ
በቀን ፡ ከሚበረው ፡ ከጠላት ፡ ፍላጻ
በክንፎቹ ፡ ጋርዶ ፡ ሸሽጎኛልና
በእርሱ ፡ እታመናለሁ ፡ ያስጥለኛል
ስሙን ፡ አውቀዋለሁ ፡ ይጋርደኛል
በመከራዬ ፡ ጊዜ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
ታማኙን ፡ አምላኬን ፡ ላመስግነው (፪x)
ክብር (፱x)
ክብር ለርሱ ፡ ይሁን (፫x) - ክብር ለርሱ ፡ ይሁን (፫x)
ክብር ለርሱ ፡ ይሁን (፫x) - ክብር ለርሱ ፡ ይሁን (፫x)
ክብር ለንጉሡ (፫x) - ክብር ለንጉሡ (፫x)
ክብር ለርሱ ፡ ይሁን (፫x) - ክብር ለርሱ ፡ ይሁን (፫x)
ክብር ለንጉሡ (፫x) - ክብር ለንጉሡ (፫x)
|