ክብር ፡ ለኢየሱስ (Kibir LeEyesus) - ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ
(Dawit Wolde)

Dawit Wolde 1.jpeg


(1)

መዝሙር ፺ ፩
(Mezmur 91)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Wolde)

ለጻድቁ ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ይሁን
የሚል ፡ ዝማሬ ፡ ከምድር ፡ ዳር ፡ ሲሰማ
እኔም ፡ ድምፄን ፡ አብሬ ፡ አነሳለሁ
ለእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ እዘምራለሁ

ቅዱሳን ፡ መላዕክቱ ፡ ባንድነት
ሌሊትና ፡ ቀንም ፡ ሚሰግዱለት
የምድር ፡ ፍጥረታት ፡ ጉዑዛን ፡ ሁሉ
ለቅዱሱ ፡ መንፈስ ፡ ይገዛሉ

ደሙን ፡ አፍስሷልና ፡ እኔን ፡ ሊገዛ
ለአዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ምስጋናው ፡ ይብዛ (፪x)

ክብር ፡ ለእግዚአብሔር
ክብር ፡ ለኢየሱስ
ክብር ፡ ለመንፈስ ፡ ቅዱስ
ሥሙ ፡ በዓለም ፡ ይንገስ (፲፬x)