ጌታ ፡ አንደተናገረ (Gieta Endetenagere) - ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ
(Dawit Wolde)

Dawit Wolde 1.jpeg


(1)

መዝሙር ፺ ፩
(Mezmur 91)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Wolde)

ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ይዋሽ ፡ ዘንድ ፡ እንደሰው ፡ አይደለምና
ላይችል ፡ ላይፈጽም ፡ ላይሞላ ፡ እንዲያው ፡ ቃል ፡ አይገባምና
እርሱ ፡ ይሁን ፡ ያለው ፡ ይሆናል ፡ ቃሉ ፡ መች ፡ መሬት ፡ ጠብ ፡ ይላል
የፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ገዢ ፡ ነው ፡ እንደወደደ ፡ ያደርጋል

የጠራኝ ፡ ጌታዬ ፡ የታመነ
ሁሉ ፡ እንደቃሉ ፡ የሆነ
ምንተስኖት ፡ የማመልከዉ
ለሀይሉ ፡ ወሰን ፡ የሌለዉ

አዝ:- ጌታ ፡ እንደተናገረ ፡ እንዲሁ ፡ ስለሚፈጽመው
ለነገ ፡ መጨነቄን ፡ ትቼ ፡ ዛሬ ፡ ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ (፪x)

አብርሃምን ፡ ከዑር ፡ ሲያወጣው ፡ ወዶ ፡ ሲመርጠው ፡ ሲጠራው
እንዲያው ፡ በከንቱ ፡ አይደለም ፡ ወደ ፡ ከነዓን ፡ የመራው
በበረከቱ ፡ ባረከው ፡ በመታዘዙ ፡ አከበረው
የተስፋ ፡ ቃሉን ፡ ፈጽሞ ፡ የትውልድ ፡ አባት ፡ አደረገው

የጠራኝ ፡ ጌታዬ ፡ የታመነ
ሁሉ ፡ እንደቃሉ ፡ የሆነ
ምንተስኖት ፡ የማመልከዉ
ለሀይሉ ፡ ወሰን ፡ የሌለዉ

ሆ ፡ ሆ ፡ ሆ (፰x)

ምንተስኖት ፡ ምንተስኖት
ምን ፡ አቅቶት ፡ ማን ፡ አግዶት
እንደወደደ ፡ ያደርጋል
ሰይጣንን ፡ ያንበረክካል (፪x)

አዝ:- ጌታ ፡ እንደተናገረ ፡ እንዲሁ ፡ ስለሚፈጽመው
ለነገ ፡ መጨነቄን ፡ ትቼ ፡ ዛሬ ፡ ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ (፪x)

አለቀ ፡ አበቃልኝ ፡ ብዬ ፡ መሰንቆዬንም ፡ ሰቅዬ
ተቆርጧል ፡ ባልኩት ፡ ጉዳይ ፡ ከተፍ ፡ አለልኝ ፡ ጌታዬ
ባህር ፡ ከፍሎ ፡ ስያሻግረኝ ፡ የረገጥኩትን ፡ ሲያወርሰኝ
ስላየሁ ፡ ደግሞ ፡ ደጋግሞ ፡ በድል ፡ ተራራ ፡ ሲያቆመኝ

ጌታ ፡ አሰራሩን ፡ አውርቼ
ስለማልቸርስ ፡ አውርቼ
ተመስገን ፡ ከማለት ፡ በቀር
ሌላ ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ልናገር (፪x)