ኢየሱስ (Eyesus) - ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ
(Dawit Wolde)

Dawit Wolde 1.jpeg


(1)

መዝሙር ፺ ፩
(Mezmur 91)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Wolde)

ሥምህን ፡ ሳስጠራ ፡ በዝማሬ
በቤትህ ፡ ስኖር ፡ እስከዛሬ
አይጠገብም ፡ ከማር ፡ ይጥማል
ሥምህ ፡ ከሥሞች ፡ ሁሉ ፡ ይልቃል
ያንተን ፡ ውለታ ፡ ነፍሴ ፡ ተረድታ
ታከብርሃለች ፡ ጠዋትና ፡ ማታ
ታከብርሃለች ፡ ቀንና ፡ ማታ

ቀናት ፡ አለፉ ፡ እንደ ፡ ጥላ
አምና ፡ ካቻምና ፡ ቀረ ፡ ከኋላ
ባሳለፍኳቸው፡ ዘመኞቼ
አፍሬ ፡ አላወቅም ፡ አንተን ፡ ጠርቼ
የጸና ፡ ክንድ ፡ ነው ፡ መሸሸጊያ
ጌታዬ ፡ ስምህ ፡ መጠለያ
ካለም ፡ ጥፋት ፡ ማምለጫ ፡ ጥላ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ አምላኬ
እኔ ፡ ከቶ ፡ አልጠግብም ፡ ሥምህን ፡ ጠርቼ
ብዙ ፡ ምስጋናህን ፡ ዘምሬ ፡ መስክሬ

አባ ፡ አባት ፡ ብሎ ፡ ማነው ፡ ያፈረ
አንተን ፡ ተማምኖ ፡ ከስሮ ፡ የቀረ
ጻድቅ ፡ ተርቦ ፡ ዘሩ ፡ ሲለምን
በታሪክ ፡ የለም ፡ አልሰማንም
ለኔስ ፡ ማትረፍ ፡ ነው ፡ ቤትህ ፡ መኖሬ
ያንተን ፡ ምስጋና ፡ መዘመሬ
ቅዱስ ፡ ሥምህን ፡ መመስከሬ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ አምላኬ
እኔ ፡ ከቶ ፡ አልጠግብም ፡ ሥምህን ፡ ጠርቼ
ብዙ ፡ ምስጋናህን ፡ ዘምሬ ፡ መስክሬ (፪x)
 
"ኢየሱስ ፡ ሥምህ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ሁሉ ፡ ዘልቆ ፡ እንደሚገባ
ነፍስንም ፡ እንደሚያረሰርስ ፡ ቁስልንም ፡ እንደሚፈውስ
መልካም ፡ መዓዛ ፡ ያለው ፡ ዘይት ፡ ነው
ለክቡር ፡ ሥምህ ፡ እዘምራለሁ"

ኢየሱስ ፡ (ኢየሱስ) ፡ ጌታዬ ፡ (ጌታዬ)
መድህኔ ፡ (መድህኔ) ፡ አመልክሃለሁ ፡ እኔ (፫x)

ሥምህ ፡ ከሥሞች ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው
ከስልጣን ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ስልጣን ፡ ያለው
በምስጋና ፡ ቃል ፡ እጠራሃለሁ ፡ ጠላቶቼን ፡ እረግጣለሁ (፫x)

ጌታዬ ፡ ሥምህ ፡ መሸሸጊያ
ከዓለም ፡ ጥፋት ፡ ማምለጫ ፡ ጥላ