እኔ ፡ የማመልከው (Enie Yemamelkew) - ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ
(Dawit Wolde)

Dawit Wolde 1.jpeg


(1)

መዝሙር ፺ ፩
(Mezmur 91)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Wolde)

የጌታን ፡ ውለታ ፡ በምን ፡ እመልሳለሁ
ዘላለም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለሁ
የአምላኬን ፡ ውለታ ፡ በምን ፡ እመልሳለሁ
ዘላለም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለሁ

ችግረኛን ፡ የሚታደግ ፡ የቆሰለን ፡ የሚፈውስ
ለታመነው ፡ ፈጥኖ ፡ የሚደርስ ፡ ሥሙ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ማዕበሉን ፡ አሳለፈኝ ፡ ወጀቡንም ፡ አሻገረን
እጄን ፡ ይዞ ፡ እየመራ ፡ እዚህ ፡ አደረሰኝ

አዝ:- እኔ ፡ የማመልከው ፡ ጌታዬ
አባት ፡ ወንድም ፡ ጓደኛዬ ፡ የጸና ፡ ስሙ ፡ መሸሸግያዬ
በፍቅሩ ፡ ተማርኬያለሁ ፡ ፍቅጄ ፡ አመልከዋለሁ
ለዘላለም ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ (፪x)

ያን ፡ ፈተና ፡ የገነነ ፡ እንደተራራ ፡ የሆነ
የአምላኬን ፡ ስም ፡ ስጠራበት ፡ እንደ ፡ ጉም ፡ ተነነ
የባሕሩም ፡ ወጀብ ፡ ከብዶ ፡ ነፍሴን ፡ በሌት ፡ አስጨንቋት
ግን ፡ ጌታዬ ፡ ምን ፡ ተስኖት ፡ ተረማመደበት

አዝ:- እኔ ፡ የማመልከው ፡ ጌታዬ
አባት ፡ ወንድም ፡ ጓደኛዬ ፡ የጸና ፡ ስሙ ፡ መሸሸግያዬ
በፍቅሩ ፡ ተማርኬያለሁ ፡ ፈቅጄ ፡ አመልከዋለሁ
ለዘላለም ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ ፡ (፪x)

የጌታን ፡ ውለታ ፡ በምን ፡ እመልሳለሁ
ዘላለም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለሁ
የአምላኬን ፡ ውለታ ፡ በምን ፡ እመልሳለሁ
ዘላለም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለሁ

እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ የማይተኛ ፡ ጠባቂዬ
በክፉ ፡ ቀን ፡ ማምለጫዬ ፡ ሥሙ ፡ መከታዬ
ይመራኛል ፡ አምነዋለሁ ፡ እርሱ ፡ ይግዛኝ ፡ እገዛለሁ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ አባት ፡ ወዴት ፡ አገኛለሁ

አዝ:- እኔ ፡ የማመልከው ፡ ጌታዬ
አባት ፡ ወንድም ፡ ጓደኛዬ ፡ የጸና ፡ ስሙ ፡ መሸሸግያዬ
በፍቅሩ ፡ ተማርኬያለሁ ፡ ፍቅጄ ፡ አመልከዋለሁ
ለዘላለም ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ ፡ (፬x)