አመሰግናለሁ (Amesegnalehu) - ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ
(Dawit Wolde)

Dawit Wolde 1.jpeg


(1)

መዝሙር ፺ ፩
(Mezmur 91)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ (ዳኒ) ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Wolde)

"ምሕረትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ እጅግ ፡ በዝቷልና
ክንድህም ፡ ለረድኤት ፡ ተዘርግቷልና
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ"

ከፍ ፡ አደርግሃለሁ ፡ አመሰግናለሁ (፬x)

ምሕረትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ እጅግ ፡ በዝቷልና
ክንድህም ፡ ለረድኤቴ ፡ ተዘርግቷልና
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ አመልክሃለሁ
ስምህን ፡ ለዘላለም ፡ እባርከዋለሁ
ከፍ ፡ አደርግሃለሁ (፪x)

ከፍ ፡ አደርግሃለሁ ፡ አመሰግናለሁ (፬x)

የዳዊት ፡ ልጅ ፡ ማረኝ ፡ ፡ ሲልህ
እጁን ፡ አንስቶ ፡ ፊትህ ፡ ተደፍቶ ፡ ሲለምንህ ፡ ስማጸንህ
አታልፈውም ፡ ያንን ፡ ምስኪን ፡ ሰው
ሙሉ ፡ ሰው ፡ አድርገህ ፡ ጤናውን ፡ ሰጥተህ ፡ ሳትፈውሰው

ምሕረትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ እጅግ ፡ በዝቷልና
ክንድህም ፡ ለረድኤቴ ፡ ተዘርግቷልና
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ አመልክሃለሁ
ስምህን ፡ ለዘላለም ፡ እባርከዋለሁ
ከፍ ፡ አደርግሃለሁ (ከፍ ፡ አደርግሃለሁ)

በዮርዳኖስ ፡ ወንዝ ፡ ዳር ፡ ቆሜ
አፍሬ ፡ አላውቅም ፡ የኤልያስ ፡ አምላክ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ የት ፡ ነህ ፡ ብዬ
ምልጃ ፡ ጸሎቴን ፡ ትመልስና
ወንዙን ፡ አሻግረህ ፡ ታቆመናለህ ፡ በምስጋና

ምሕረትህ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ እጅግ ፡ በዝቷልና
ክንድህም ፡ ለረድኤቴ ፡ ተዘርግቷልና
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ አመልክሃለሁ
ስምህን ፡ ለዘላለም ፡ እባርከዋለሁ
ከፍ ፡ አደርግሃለሁ (ከፍ ፡ አደርግሃለሁ)

ከፍ ፡ አደርግሃለሁ ፡ አመሰግናለሁ (፰x)