የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ (Yerasie Neger Selalteqemegn) - ዳዊት ፡ ሞላልኝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ ሞላልኝ
(Dawit Molalegn)

Dawit Molalegn 1.png


(1)

ተባረረ
(Tebarere)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ሞላልኝ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Molalegn)

አዝ፦ የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ
ዋጋ ፡ ተምኜ ፡ ወጥቻለሁኝ
ጌታን ፡ ማገልገል ፡ ትርፍ ፡ አለውና
ጥማዱን ፡ ስበር ፡ ስበር ፡ ውጣና

የእኔ ፡ የራሴ ፡ ባልሆነ ፡ ነገር
ብዙ ፡ ቆየሁኝ ፡ ያኔ ፡ ስቸገር
ዛሬ ፡ ዛሬማ ፡ በራልኝና
ድንቁን ፡ ራዕይ ፡ አየሁኝና
ሁሉንም ፡ ነገር ፡ ለጌታ ፡ ትቼ
እፎይ ፡ አረፍኩኝ ፡ ተማቻችቼ (፬x)

አዝ፦ የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ
ዋጋ ፡ ተምኜ ፡ ወጥቻለሁኝ
ጌታን ፡ ማገልገል ፡ ትርፍ ፡ አለውና
ጥማዱን ፡ ስበር ፡ ስበር ፡ ውጣና

ታማኝ ፡ አድርጐ ፡ ስለቆጠረኝ
ለአገልግሎቱ ፡ ጌታ ፡ የሾመኝ
ሞኞች ፡ ቢነቅፉኝ ፡ ቢዘብቱብኝ
ትቼ ፡ የመጣሁ ፡ ባሪያው ፡ እኮ ፡ ነኝ
እየታገሰ ፡ ብርቱ ፡ የሚያደርገው
የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ ነው (፬x)

አዝ፦ የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ
ዋጋ ፡ ተምኜ ፡ ወጥቻለሁኝ
ጌታን ፡ ማገልገል ፡ ትርፍ ፡ አለውና
ጥማዱን ፡ ስበር ፡ ስበር ፡ ውጣና

ከአባቴ ፡ ቤት ፡ አስወጣኝ ፡ ጌታ
ወዳሳየኝ ፡ ሄድኩ ፡ ሳላመነታ
እርሱን ፡ ታምኜ ፡ ስለወጣሁኝ
እረሃቡ ፡ ጸና ፡ ጥሬ ፡ ስላለኝ
ዘርህ ፡ እንደአሸዋ ፡ ይበዛል ፡ እንዳለው
ቃሉን ፡ ፈጸመው ፡ ተዓምረኛ ፡ ነው (፬x)

አዝ፦ የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ
ዋጋ ፡ ተምኜ ፡ ወጥቻለሁኝ
ጌታን ፡ ማገልገል ፡ ትርፍ ፡ አለውና
ጥማዱን ፡ ስበር ፡ ስበር ፡ ውጣና

እናት ፡ አባቴ ፡ እረስተውኛል
ቸሩ ፡ እግዚአብሔር ፡ ተቀብሎኛል
የሁሉ ፡ ታናሽ ፡ የበግ ፡ እረኛ
ታላቅ ፡ እያለ ፡ መርጦ ፡ ቀባኛ
እርሱ ፡ ሲያጸድቅ ፡ ማን ፡ ይቃወማል
መቼ ፡ በቁመት ፡ ልብም ፡ ይታያል (፬x)

አዝ፦ የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ
ዋጋ ፡ ተምኜ ፡ ወጥቻለሁኝ
ጌታን ፡ ማገልገል ፡ ትርፍ ፡ አለውና
ጥማዱን ፡ ስበር ፡ ስበር ፡ ውጣና