ትመቸኛለህ (Temechegnaleh) - ዳዊት ፡ ሞላልኝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ ሞላልኝ
(Dawit Molalegn)

Dawit Molalegn 1.png


(1)

ተባረረ
(Tebarere)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 9:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ሞላልኝ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Molalegn)

አዝከአንተው ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ
ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x)
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ትመቸኛለህ ፡ ጌታ ፡ አሃሃ
ትመችኛለህ ፡ ኢየሱስ
ትመቸኛለህ ፡ አሃ (፪x)

ወደ ፡ ላይ ፡ ብወጣ ፡ አንተ ፡ በዚያ ፡ አለህ
ወደታች ፡ ብወድቅም ፡ ቀድመህ ፡ ትገኛለህ
ከአንተ ፡ ተሸሽቶ ፡ ወዴት ፡ ይደረሳል
ከአንተው ፡ ተስማምቶ ፡ መኖር ፡ ይሻለኛል

አዝከአንተው ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ
ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x)
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ትመቸኛለህ ፡ ጌታ ፡ አሃሃ
ትመችኛለህ ፡ ኢየሱስ
ትመቸኛለህ ፡ አሃ (፪x)

መልካም ፡ ለመሰለኝ ፡ በዓይኔ ፡ ላየሁት
ፈቃዴን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤን ፡ ከሰጠሁት
ጌታዬ ፡ ይቅር ፡ በለኝ ፡ አንተን ፡ ለበደልኩት
ቤትህ ፡ ይሻለኛል ፡ ሰላም ፡ የሞላበት

አዝከአንተው ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ
ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x)
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ትመቸኛለህ ፡ ጌታ ፡ አሃሃ
ትመችኛለህ ፡ ኢየሱስ
ትመቸኛለህ ፡ አሃ (፪x)

ወጥቼ ፡ ነበረ ፡ ድርሻዬን ፡ ሰጥተኸኝ
ተመልሼ ፡ መጣሁ ፡ ጨርሼው ፡ አልቆብኝ
ፊትህ ፡ አልጠቆረ ፡ በርህ ፡ አልተዘጋብኝ
አይደለም ፡ እንደልጅ ፡ ባሪያ ፡ አድርገህ ፡ ግዛኝ

አዝከአንተው ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ
ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x)
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ትመቸኛለህ ፡ ጌታ ፡ አሃሃ
ትመችኛለህ ፡ ኢየሱስ
ትመቸኛለህ ፡ አሃ (፪x)

ለጊዜው ፡ ከሚገኝ ፡ ከኃጢአት ፡ ደስታ
ሞት ፡ ከገነነበት ፡ ግርግር ፡ ሁካታ
የሰጠኸኝ ፡ ሰላም ፡ የቤትህ ፡ አርካታ
በባዶ ፡ ያዘልላል ፡ ስሙ ፡ የእኔ ፡ ጌታ

አዝከአንተው ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ
ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x)
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ
ትመቸኛለህ ፡ ጌታ ፡ አሃሃ
ትመችኛለህ ፡ ኢየሱስ
ትመቸኛለህ ፡ አሃ (፪x)