Dawit Molalegn/Tebarere/Gerem Yelegnal

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እግዚአብሔር ግርም ይለኛል
እግዚአብሔር ድንቅ ይለኛል(፪x     <   መልካምነው(፪x)     

 መንገድ ላይ ጥሎኝ አልሄደም
 ደከመኝ ሰለቸኝ አላለም                
ቀንና ሌሊቱ ትልቅ ነህ ይሉታል
መላዕክት ፍጥረቱ ሁሉ ያመልኩታል
አባቶች አምልከው አክብረውት አልፈዋል
በእኔና በቤቴም ጌታ ይመለካል።

አዝማች  
         

እንደሌዊ አይደል እንዴት ትቶኝ ያልፋል ልክ እንደ ካህኑ መች ያፈገፍጋል ደጉ ጌታ እየሱስ እጁን ይዘረጋል ቁስሌን በዘይቱ ቀብቶ ያነሳኛል።

አዝማች
 
 ላቆምከው አልሰግድም ብዬ
 አልቀረሁም እሳት ዉስጥ ተጥዬ
 ይታመናል ታማኝ ነው ጌታዬ(፬×} 
ሰባት እጥፍ ሲነድ ወርውረው ጣሉኝ
የአማልክት አምላክ እዛው አገኘኝ
ኧረ እንዴት ተረፈ ከእሳት ያላችሁ
ከመከራው በፊት ኢየሱስ ያግኛቹ።
 እግዚአብሔር ግርም ይለኛል
 እግዚአብሔር ድንቅ ይለኛል (፪x) 
 መልካም ነው (፪x )