From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ዞር ዞር ዞር ዞርበል ጠላቴ
ጌታ ፈቶኛል ከእስራቴ
አንዴ ፈቶኛል አልመለስም
እጄን ለጠላት ፈፅሞ አልሰጥም
እለፍ ብሎኛል ጌታዬ አልያዝም
ሂድ ብሎኛል የሱሴ አልዘገይም/2
አውቆ ያክፉ እራዕይ አንዳለኝ
ወጥመድ ዘርግቶ አታልፍም ቢለኝ
ወጥመዱን ሰብሮ ጌታዬ ሂድ እለፍ አለኝ
በጌትነቱ እየሱሴ እኔን አኮራኝ
አኮራኝ ጌታዬ/4
እለፍ ብሎኛል ጌታዬ አልያዝም
ሂድ ብሎኛል የሱሴ አልዘገይም/2
ከቀድሞ ይልቅ ዮርዳኖስ ሞልቶ
ተስፋ ያለውን ህዝብ አስፈራርቶ
ልክ እንደክምር ባህሩ በቃሉ ያቆመው
ተስፋን የሰጠው እግዚአብሔር የታመነነ ነው
ታመኝ ነው ጌታዬ/4
እለፍ ብሎኛል ጌታዬ አልያዝም
ሂድ ብሎኛል የሱሴ አልዘገይም/2
ላምላኬ እንዳልሰግድ ሲከታተሉኝ
ሰበብ ፈልገው ጉድጓድ ከተቱኝ
ላንበሶች ሰቷቸው ተንከባከቡኝ
መላኩን ልኮ ጌታዬ ከሞት አዳነኝ
አዳነኝ ጌታዬ/4
እለፍ ብሎኛል ጌታዬ አልያዝም
ሂድ ብሎኛል የሱሴ አልዘገይም/2
|