From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር
ማነው ፡ ሚከራከር ፡ ማነው ፡ ሚለው ፡ ቅር (፫x)
ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ
ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)
ሰው ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ ይከራከራል
ጌታውን ፡ ለማምለክ ፡ ጥቅስ ፡ ያወጣጣል
አንዱ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ሲል ፡ ሌላው ፡ እንዲያ ፡ ይላል
አምልኮ ፡ ለጌታ ፡ ነው ፡ ሰውን ፡ ምን ፡ ነክቶታል
በመንፈስ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ እየሱስ ፡ ተመችቶታል
(የእኔ ፡ ጌታ) አምላኬ ፡ ተቀብሎታል
እየሱስ ፡ ተመችቶታል (ኢየሱስ) ፡ አምላኬ ፡ ተቀብሎታል
አዝ፦ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር
ማነው ፡ ሚከራከር ፡ ማነው ፡ ሚለው ፡ ቅር (፫x)
ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ
ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)
ጡት ፡ ከሚጠቡት ፡ ከህፃናቱ
ምስጋናን ፡ ለእርሱ ፡ ማዘጋጀቱ
ገብቶት ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አይደለም ፡ በከንቱ
አምልኮ ፡ ምስጋናቸው ፡ ገብቷል ፡ ፀባኦቱ
ለእኛ ፡ አይግባን ፡ እንጂ ፡ ወዶታል ፡ ይሄ ፡ ክንዴ ፡ ብርቱ
ወዶታል ፡ እየሱስ ፡ ብርቱ (፫x)
አዝ፦ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር
ማነው ፡ ሚከራከር ፡ ማነው ፡ ሚለው ፡ ቅር (፫x)
ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ
ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)
ብልቃጡን ፡ ሰብራ ሽቶ ፡ አፈሰሰች
ድሮ ፡ በሚያውቋት ፡ እየተተቸች
የጌታዋን ፡ እግር ፡ መሳሟን ፡ ቀጠለች
እየሱስ ፡ ተደነቀ ፡ በሰላም ፡ ሂጂ ፡ አላት
በተቺዎቿ ፡ ፊትም ፡ ጌታዬ ፡ መሰከረላት
(የእኔ ፡ ጌታ) አባቴ ፡ ልክ ፡ ነሽ ፡ አላት
ኢየሱስ (ኢየሱስ) ፡ መሰከረላት ፡ አባቴ ፡ መሰከረላት
አዝ፦ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር
ማነው ፡ ሚከራከር ፡ ማነው ፡ ሚለው ፡ ቅር (፫x)
ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ
ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)
እኔን ፡ ያዳነኝ ፡ የደሙ ፡ ሚስጥር
ገብቶኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የውዴ ፡ ፍቅር
ምስጋና ፡ አምልኮዬ ፡ ለጌታዬ ፡ ክብር
ንገሥ ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ ፡ ክበር ፡ ጌታ ፡ እየሱስ
አምልኮ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ለሌላ ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ
(ለመላዕክት) ለሌላ ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ
(ለሰማዕቶት) ለሌላ ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ
(ለመላዕክት) ለሌላ ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ
(ለሰማዕቶት
አዝ፦ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር
ማነው ፡ ሚከራከር ፡ ማነው ፡ ሚለው ፡ ቅር (፫x)
ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ
ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)
|