From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ህዝቡን የሚያስለቅስ በሞት የሚቀጣ
ሲያጣ ባያሟላ ግብር ባያመጣ
የናዝሬቱ የሱስ ገናናው ሲመጣ
ስራው ፈረሰበት ይኸው ግራ ገባው
የሚገባበት አጣ/4
እየሱስ ሃይለኛ
ባለም ላይ ብቸኛ
ጠላቴ ማይችለው
ገናና ስም ያለው
ጌታን ተጣራ እንጂ ክፉን እንዳትፈራ
በሁሉም ስፍራ ላይ አለ ካንተ ጋራ/2
ህዝቡን የሚያስለቅስ በሞት የሚቀጣ
ሲያጣ ባያሟላ ግብር ባያመጣ
የናዝሬቱ የሱስ ገናናው ሲመጣ
ስራው ፈረሰበት ይኸው ግራ ገባው
የሚገባበት አጣ/4
እኔ መቼ እፈራለሁ
ጌታን ይዤ እኮራለው
በጣላት ላይ እጫማለው
ካሸናፊዎችሁ ሁሉ አስመልጦኛል
እባብና ጊንጡን እርገጠው ብሎኛል/2
ህዝቡን የሚያስለቅስ በሞት የሚቀጣ
ሲያጣ ባያሟላ ግብር ባያመጣ
የናዝሬቱ የሱስ ገናናው ሲመጣ
ስራው ፈረሰበት ይኸው ግራ ገባው
የሚገባበት አጣ/4
ስድስት ክንድ ከስንዝር
ነኝ ብሎ ሲፎክር
ሰውን አስድነቀ
በጠጠር ወደቀ
ጠላቴ ጉልበቱ አፉ ላይ እኮ ነው
ውሻ ነኝ ይልሃል አንበሳ ነኝ ያለው/2
ህዝቡን የሚያስለቅስ በሞት የሚቀጣ
ሲያጣ ባያሟላ ግብር ባያመጣ
የናዝሬቱ የሱስ ገናናው ሲመጣ
ስራው ፈረሰበት ይኸው ግራ ገባው
የሚገባበት አጣ/4
እኔን ሊጥል ሚፎክረው
በዙሪያዬ የሚዞረው
ጉድጓድ ለኔ ሚቆፍረው
ጋሻ ከለላዬ እግዚአብሔር እኮ ነው
በቆፈረው ጉድጓድ ጠላቴን ጨመረው/2
ህዝቡን የሚያስለቅስ በሞት የሚቀጣ
ሲያጣ ባያሟላ ግብር ባያመጣ
የናዝሬቱ የሱስ ገናናው ሲመጣ
ስራው ፈረሰበት ይኸው ግራ ገባው
የሚገባበት አጣ/4
|