እንዴት ፡ ሰው ፡ ሳያነብ (Endiet Sew Sayaneb) - ዳዊት ፡ ሞላልኝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ ሞላልኝ
(Dawit Molalegn)


(2)

አትታማ
(Atetama)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ሞላልኝ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Molalegn)

ላምልከው (፭x)
በመንፈስ ፡ ሁኑና ፡ ጌታን ፡ አመስግኑት (አመስግኑት)
በመንፈስ ፡ ሁኑና ፡ ለእርሱ ተቀኙለት
ከሞት ፡ ያስመለጠኝ ፡ እየሱሴ ፡ በሉት (፪x)
ኢየሱሴ ፡ በሉት

ጌታን ፡ ማገልገሉ ፡ ምን ፡ ጠቀመው ፡ ሲሉኝ
ጌታን ፡ መከተሉ ፡ ምን ፡ ረባው ፡ ሲሉኝ
የተፃፈልኝን ፡ ቃል ፡ አነበብኩኝ
እንዳገለግለው ፡ የባሰ ፡ አበረታታኝ

በምድር ፡ መቶ ፡ እጥፍ (አሜን)
በሰማይ ፡ ቤት ፡ አለኝ
በምድር ፡ መቶ ፡ እጥፍ (አሜን)
በሰማይ ፡ ቤት ፡ አለኝ
በሰማይ ፡ ቤት ፡ አለኝ

በመንፈስ ፡ ሁኑና ፡ ጌታን ፡ አመስግኑት (አመስግኑት)
በመንፈስ ፡ ሁኑና ፡ ለእርሱ ተቀኙለት
ከሞት ፡ ያስመለጠኝ ፡ እየሱሴ ፡ በሉት (፪x)
ኢየሱሴ ፡ በሉት

እምነት ፡ ከመስማት ፡ ነው
መስማትም ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ነው
እንዴት ፡ ሰው ፡ ሳያነብ ፡ ከአያቱ ፡ ይወርሳል
እውር ፡ እውርን ፡ ሰው ፡ ወዴት ፡ ይመራዋል
ተያይዞ ፡ ገደል ፡ በለው ፡ ኃላን ፡ ይቆጭሃል

እውነቱን ፡ ልንገርህ (እውነቱን)፡ እየሱስ ፡ ያድናል (አሳምሮ)
እውነቱን ፡ ልንገርህ (እውነቱን)፡ እየሱስ ፡ ያድናል (አሳምሮ)
ኢየሱስ ፡ ያድናል

በመንፈስ ፡ ሁኑና ፡ ጌታን ፡ አመስግኑት (አመስግኑት)
በመንፈስ ፡ ሁኑና ፡ ለእርሱ ተቀኙለት
ከሞት ፡ ያስመለጠኝ ፡ እየሱሴ ፡ በሉት (፪x)
ኢየሱሴ ፡ በሉት

ልቤን ፡ ስለጣልኩኝ ፡ ብሉይ ፡ ኪዳን ፡ ላይ
በጥላው ፡ ረክቼን ፡ አዲስን ፡ ሳላይ
በእራሴ ፡ እንዳልወስን ፡ ነበሩኝ ፡ ከልካይ
ይሉኝታው ፡ ለቀቀኝ (እሰይ) ፡ እየሱስን ፡ ሳይ

ይኸው ፡ ስንት ፡ አመቴን (ሳይሰለቸኝ) ፡ ሆንኩኝ ፡ የእርሱ ፡ አገልጋይ (ተመችቶኝ)
ይኸው ፡ ስንት ፡ አመቴን (ሳይሰለቸኝ) ፡ ሆንኩኝ ፡ የእርሱ ፡ አገልጋይ (ተመችቶኝ)
ሆንኩኝ ፡ የሱ ፡ አገልጋይ

በመንፈስ ፡ ሁኑና ፡ ጌታን ፡ አመስግኑት (አመስግኑት)
በመንፈስ ፡ ሁኑና ፡ ለእርሱ ተቀኙለት
ከሞት ፡ ያስመለጠኝ ፡ እየሱሴ ፡ በሉት (፪x)
ኢየሱሴ ፡ በሉት