From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ዳዊት ፡ ሞላልኝ (Dawit Molalegn)
|
|
፪ (2)
|
አልበም (Vol 2)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
|
ቁጥር (Track):
|
፯ (7)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የዳዊት ፡ ሞላልኝ ፡ አልበሞች (Albums by Dawit Molalegn)
|
|
ደጋሚዎች ፡ ተሰብስበው ፡ ሲያሟርቱ ፡ ይሙት ፡ ብለው ፡ አጫጭሰው
ይኸው ፡ አለሁ ፡ እስከ ፡ ዛሬ
እንኳን ፡ ብሞት ፡ ተከብሬ (፪x)
ሰይጣን ፡ በዙሪያዬ ፡ የሚዞረው
ካልገደልኩት ፡ ብሎ ፡ ሚፎክረው
ጠላቴ ፡ ያልገባው ፡ አንድ ፡ ነገር
እግዚአብሔር ፡ ብሎኛል ፡ አትሸበር
የጌታ ፡ ነኝ ፡ እኔስ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ ፈፅሞ ፡ ማልገኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ እኔስ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ ጭራሽ ፡ የማልገኝ (፪x)
ከቀስት ፡ ፊት ፡ ያመልጡ ፡ ዘንድ ፡ ለሚፈሩህ ፡ ምልክትን ፡ ሰጠሀቸው
አንዴ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጥኩት
ብለሀቸው ፡ እስኪ ፡ ንኩት (፪x)
ሰይጣን ፡ በዙሪያዬ ፡ የሚዞረው
ካልገደልኩት ፡ ብሎ ፡ ሚፎክረው
ጠላቴ ፡ ያልገባው ፡ አንድ ፡ ነገር
እግዚአብሔር ፡ ብሎኛል ፡ አትሸበር
የጌታ ፡ ነኝ ፡ እኔስ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ ፈፅሞ ፡ ማልገኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ እኔስ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ ጭራሽ ፡ የማልገኝ (፪x)
ፃድቅ ፡ ሲራብ ፡ ዘሩም ፡ ሲለምን ፡ አልሰማሁም ፡ አላየሁም ፡ ሲቸግር
ምንም ፡ ባይኖር ፡ በጎተራቸው
አያስርብም ፡ አምላካቸው (፪x)
ሰይጣን ፡ በዙሪያዬ ፡ የሚዞረው
ካልገደልኩት ፡ ብሎ ፡ ሚፎክረው
ጠላቴ ፡ ያልገባው ፡ አንድ ፡ ነገር
እግዚአብሔር ፡ ብሎኛል ፡ አትሸበር
የጌታ ፡ ነኝ ፡ እኔስ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ ፈፅሞ ፡ ማልገኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ እኔስ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ ጭራሽ ፡ የማልገኝ (፪x)
|