አንተማ ፡ አትታማ (Antema Atetama) - ዳዊት ፡ ሞላልኝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ ሞላልኝ
(Dawit Molalegn)

Dawit Molalegn 2.png


(2)

አትታማ
(Atetama)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ሞላልኝ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Molalegn)

ቀኑ ፡ ሲከፋ ፡ ጊዜው ፡ ሲረዝም
ጌታ ፡ ትቶኛል ፡ ብዬ ፡ ስቆዝም
በጊዜው ፡ ደርሰህ ፡ ውብ ፡ አድርገሃል
ድንቅ ፡ አድራጊ ፡ ነህ ፡ አንተን ፡ ማን ፡ ያምሃል

አዝአንተማ (፫x) ፡ አትታማ (፪x)
ጌታማ ፡ አይታማ (፬x)

ተስፋው ፡ ሲዘገይ ፡ ሲጨልምብኝ
ብዬው ፡ ነበረ ፡ ጌታን ፡ ግደለኝ
ሌቱ ፡ ሲነጋ ፡ ሁሉም ፡ ሲቀየር
ብዬ ፡ ፀለይኩ ፡ እድሜዬን ፡ ጨምር

አዝአንተማ (፫x) ፡ አትታማ (፪x)
ጌታማ ፡ አይታማ (፬x)

የታመንንበት ፡ ተስፋ ፡ ያረግነው
ሞተብን ፡ ብለው ፡ አዝነው ፡ ጠውልገው
ድንገት ፡ ተገልጦ ፡ መካከላቸው
በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ አሳፈራቸው

አዝአንተማ (፫x) ፡ አትታማ (፪x)
ጌታማ ፡ አይታማ (፬x)

ለሚበላና ፡ ለሚጠታዉ
እንዴት ፡ ይታማል ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው
ንፋስ ፡ ሳይታይ ፡ ዝናብም ፡ ሳይኖር
ምንጭን ፡ ያፈልቃል ፡ ከደረቅ ፡ ምድር

አዝአንተማ (፫x) ፡ አትታማ (፪x)
ጌታማ ፡ አይታማ (፬x)