አምልኮ ፡ ለጌታ ፡ ነው (Amleko Legieta New) - ዳዊት ፡ ሞላልኝ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳዊት ፡ ሞላልኝ
(Dawit Molalegn)

Dawit Molalegn 2.png


(2)

አትታማ
(Atetama)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 7:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ሞላልኝ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Molalegn)

እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር
ማነው፡ የሚከራከር ፡ ማነው ፡ የሚለው ፡ ቅር
ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ
ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)

ሰው ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ ይከራከራል
ጌታን ፡ ለማምለክ ፡ ጥቅስ ፡ ያወጣጣል
አንዱ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ሲል ፡ ሌላው ፡ እንዲያ ፡ ይላል
አምልኮ ፡ ለጌታ ፡ ነው ፡ ሰውን ፡ ምን ፡ ነክቶታል
በመንፈስ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ እየሱስ ፡ ተመችቶታል
አምላኬ ፡ ተቀብሎታል

እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር
ማነው፡ የሚከራከር ፡ ማነው ፡ የሚለው ፡ ቅር
ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ
ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)

ጡት ፡ ከሚጠቡት ፡ ከህፃናቱ
ምስጋናን ፡ ለእርሱ ፡ ማዘጋጀቱ
ገብቶት ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አይደለም ፡ በከንቱ
አምልኮ ፡ ምስጋናችን ፡ ገብቷል ፡ ፀባኦቱ
ለእኛ ፡ አይግባን ፡ እንጂ ፡ ወዶታል ፡ ይሄ ፡ ክንዴ ፡ ብርቱ
ወዶታል ፡ እየሱስ ፡ ብርቱ

እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር
ማነው፡ የሚከራከር ፡ ማነው ፡ የሚለው ፡ ቅር
ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ
ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)

ብልቃጡን ፡ ሰብራ ሽቶ ፡ አፈሰሰች
ድሮ ፡ በሚያውቋት ፡ እየተተቸች
የጌታዋን ፡ እግር ፡ መጠቧን ፡ ቀጠለች
እየሱስ ፡ ተደነቀ ፡ በሰላም ፡ ሂጂ ፡ አላት
በተቺዎቿ ፡ ፊትም ፡ ጌታዬ ፡ መሰከረላት

እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር
ማነው፡ የሚከራከር ፡ ማነው ፡ የሚለው ፡ ቅር
ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ
ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)

እኔን ፡ ያዳነኝ ፡ የደሙ ፡ ሚስጥር
ገብቶኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የውዴ ፡ ፍቅር
ምስጋና ፡ አምልኮዬ ፡ ለጌታዬ ፡ ክብር
እኔስ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ ፡ ክበር ፡ ጌታ ፡ እየሱስ
አምልኮ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ፡ ለሌላ ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ
ለመላእት ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ
ለሰማዕታት ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ

እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር
ማነው፡ የሚከራከር ፡ ማነው ፡ የሚለው ፡ ቅር
ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ
ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)