አለ ዳኛ (Ale Dagna) - ዳዊት ፡ ሞላልኝ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳዊት ፡ ሞላልኝ
(Dawit Molalegn)

Dawit Molalegn 2.png


(2)

Atetama
(Atetama)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ሞላልኝ ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Molalegn)

ቀድሞ እንዲጠፋ እንዳይተርፍ
ክፉ አውሬ በላው ባሉት አፍ
ደግሞ መክበሩን አውርተው
ሰግደው አፀኑት ግብፅ ሄደው

የዋህን ህልመኛን አልሰማ
ስለመሞቱ ሲታማ
ሊገሉት ፀሃይ ስትጠልቅ
ህልመኛው ወጣ ሲጠበቅ
ጣልቃ ሚገባ ሚያስመልጥ
ክፉን ለበጎ የሚለውጥ

አለ ዳኛ/6

ትንሹ የፍሬ ዛፍ
ሴጣን በውንድም ሊቀጥፍ
ጌታ ለቃሉ ታማኝ ነው
በባዕድ ምድር ላይ ሾመው

የዋህን ህልመኛን አልሰማ
ስለመሞቱ ሲታማ
ሊገሉት ፀሃይ ስትጠልቅ
ህልመኛው ወጣ ሲጠበቅ
ጣልቃ ሚገባ ሚያስመልጥ
ክፉን ለበጎ የሚለውጥ

አለ ዳኛ/6

ጌታ የጠራው አገልጋይ
ወድቆ አይቀርም መንገድ ላይ
በቃ ሲል ጌታ መከራው
መፍትሄ ያለው እርሱ ነው

የዋህን ህልመኛን አልሰማ
ስለመሞቱ ሲታማ
ሊገሉት ፀሃይ ስትጠልቅ
ህልመኛው ወጣ ሲጠበቅ
ጣልቃ ሚገባ ሚያስመልጥ
ክፉን ለበጎ የሚለውጥ

አለ ዳኛ/6

ባገር በምርዱ ሲያወሩ
ሞቷል እያለ መንደሩ
መርዶ እራሳቸው አውርተው
ደግሞ ጨረሱ አልቅሰው

የዋህን ህልመኛን አልሰማ
ስለመሞቱ ሲታማ
ሊገሉት ፀሃይ ስትጠልቅ
ህልመኛው ወጣ ሲጠበቅ
ጣልቃ ሚገባ ሚያስመልጥ
ክፉን ለበጎ የሚለውጥ

አለ ዳኛ/6