እፈልግሃለሁ (Efelegehalehu) - ዳንኤል ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳንኤል ፡ ጥላሁን
(Daniel Tilahun)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ነጠላ
(Single)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 8:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Tilahun)

እጄን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ ፡ ለአንተ ፡ አነሳለሁ
ርሃቤም ፡ ጥማቴም ፡ ናፍቆቴም ፡ አንተን ፡ ነው
በሕይወቴ ፡ አክብረው ፡ እየሱስን ፡ አድምቀው
ጌታ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እፈለግሃለሁ

እፈልግሃለሁ (8x)

ሕይወቴም ፡ ኑሮዬም ፡ ይሁን ፡ ያለህበት
አንተ ፡ የምትመራው ፡ ሁሌ ፡ የምታዝበት
መኖር ፡ አልፈልግም ፡ እንዲሁ ፡ በመላ
በዘመኔ ፡ አይግዛኝ ፡ ማንም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ

እፈልግሃለሁ (8x)

ፍቅርህን ፡ በልቤ ፡ በውስጤ ፡ አፈሰስከው
ወደ ፡ እውነት ፡ ልትመራኝ ፡ ከላይ ፡ የተላከው
ስህተት ፡ የማያውቅሀ ፡ አስተማሪዬ ፡ ነህ
ከምንም ፡ ከማንም ፡ ትበልጥብኛለህ

እፈልግሃለሁ (8x)

ያለ ፡ አንተ ፡ መገኘት ፡ ሕይወት ፡ ጣዕም ፡ የለውም
ብበላም ፡ ብጠጣም ፡ ከቶ ፡ አያጠግበኝም
ልቤን ፡ የምትሞላው ፡ በሃሴት ፡ በደስታ
እፈልግሃለሁ ፡ ጥዋት ፡ ሳልል ፡ ማታ
ያለ ፡ አንተ ፡ መገኘት ፡ ሕይወት ፡ ጣዕም ፡ የለውም
ሁሉን ፡ እንኳን ፡ ባገኝ ፡ ከቶ ፡ አያረካኝም
ውስጤን ፡ የምትሞላው ፡ በክብርህ ፡ በደስታህ
እፈልግሃለሁ ፡ ጥዋት ፡ ሳልል ፡ ማታ

እጄን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ ፡ ለአንተ ፡ አነሳለሁ
ርሃቤም ፡ ጥማቴም ፡ ናፍቆቴም ፡ አንተን ፡ ነው
በሕይወቴ ፡ አክብረው ፡ እየሱስን ፡ አድምቀው
ጌታ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እፈለግሃለሁ

እፈልግሃለሁ (8x)