የማይለዋወጥ (Yemayelewawet) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 6.jpg


(6)

የሰው ፡ እጅ ፡ የሌለበት
(Yesew Ej Yelielebet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

 
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ብቻ

አዝነገር ፡ እንደነበረ ፡ እንዳለ ፡ አይቀርም (፪x)
የማይለዋወጥ ፡ የማይቀያየር
ጸንቶ ፡ የሚኖረው
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

ዝና ፡ ክብር ፡ ቋሚ ፡ አይደለም
ሃብት ፡ አያኖር፡ ለዘለዓለም
ዓለም ፡ መልኳ ፡ ተለዋጭ ፡ ነው
ያው ፡ የሆነው ፡ ክርስቶስ ፡ ነው
ሕይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

አዝነገር ፡ እንደነበረ ፡ እንዳለ ፡ አይቀርም (፪x)
የማይለዋወጥ ፡ የማይቀያየር
ጸንቶ ፡ የሚኖረው
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

ትላንት ፡ ዛሬም ፡ ለዘለዓለም
ያው ፡ የሆነው ፡ ቤዛ ፡ ለዓለም
ማይለወጥ ፡ ማያረጀው
ጌታ ፡ ብቻ ፡ የማይሞተው
ትንሳኤ ፡ ሕይወት ፡ ነው

አዝነገር ፡ እንደነበረ ፡ እንዳለ ፡ አይቀርም (፪x)
የማይለዋወጥ ፡ የማይቀያየር
ጸንቶ ፡ የሚኖረው
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

ፀሐይ ፡ ብርሃን ፡ ስትከለክል
ጨረቃዋም ፡ ደም ፡ ስትመስል
ዓለም ፡ አላት ፡ መጨረሻ
ያለ ፡ ሚኖር ፡ ጌታ ፡ ብቻ
የዘለዓለም ፡ አምባ

አዝነገር ፡ እንደነበረ ፡ እንዳለ ፡ አይቀርም (፪x)
የማይለዋወጥ ፡ የማይቀያየር
ጸንቶ ፡ የሚኖረው
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

"እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ብቻ (፬x)"