From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ኦሆ
ጽኑ ፡ መሰረቴ ፡ የነፍሴ ፡ መከታ
የራራልኝ ፡ ቀድሞ ፡ በፍቅሩ ፡ የሳበኝ
ጨለማዬን ፡ ገፎጭ ፡ በብርሃን ፡ ያኖረኝ
ቅኔን ፡ ጨመረልኝ ፡ በአፌ
ለክብሩ ፡ እንድዘምር ፡ ከልቤ
ምሥጋናውን ፡ ደግሞ ፡ እንዳወራ
አብሬ ፡ እንዳመልከው ፡ ከቅዱሳን ፡ ጋራ
ከአሪያም ፡ ወረደ ፡ መንፈሱ
ልቤን ፡ አደረገው ፡ መቅደሱ
አቤት ፡ የአምላክ ፡ ፍቅር ፡ ምህረቱ
ኢኸው ፡ ልጅ ፡ አደረገኝ ፡ እንድኖር ፡ በቤቱ
ከቁጥር ፡ ያለፈ ፡ ቸርነት ፡ ሠማያዊ ፡ ፀጋን ፡ አሄ
አምላኬ ፡ ሰጥቶኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ሕይወት
ማዳኑን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ገለጠ
በደሙ ፡ ቀደሰኝ ፡ አሄ
ኢየሱስ ፡ ሕይወቴን ፡ መልካም ፡ አደረገ
ምድር ፡ እልል ፡ ትበል ፡ ለንጉሡ
ሠማይም ፡ ያጨብጭብ ፡ ለቅዱሱ
ሁሉንም ፡ በኃይሉ ፡ የፈጠረው
የዘለዓለም ፡ ዓለም ፡ መንግሥት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ማዳኑን ፡ ልዘምር ፡ ከፍ ፡ ላድርገው
ከምርጦቹ ፡ ጋራ ፡ ላመስግነው
የጠለቀ ፡ ፍቅሩንም ፡ ልናገር
ከሠማይ ፡ በምድር ፡ ታላቅ ፡ ስሙ ፡ ይክበር
ፍቅሩን ፡ አፈሰሰ ፡ ማዳኑን ፡ ገለጠ ፡ እህ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቶ ፡ ምህረቱን ፡ አወጀ
እርሱን ፡ ያመነች ፡ ነፍ ፡ በሕይወት ፡ ትኖር ፡ ዘንድ
ቤዛ ፡ ለዓለሙ ፡ ሆነ ፡ የኀጢአት ፡ መሥዋዕት
ሞትን ፡ ያሸነፈ ፡ ግድለኛ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ ፡ ኃይለኛ
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ አንበሳ ፡ ምሥጋና ፡ የሚገባው ፡ ክብርና ፡ ሙገሳ
የጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ግርማዊ ፡ መንግሥት ፡ ከላይ ፡ ነው ፡ ሠማያዊ
ፍጥረት ፡ በመገዛት ፡ የሚያከብረው ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
አቻ ፡ ይገኝለት ፡ መውደዱ ፡ አቤት ፡ የአምላክ ፡ ፍቅር ፡ አሄ
ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ምህረት ፡ ተገዝቶ ፡ አሄ
ምክሩ ፡ ከሰው ፡ ጥበብ ፡ የላቀ
ማስተዋሉ ፡ ረቂቅ ፡ አሄ
ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታችን ፡ በክብር ፡ የደመቀ
ሃሌሉያ ፡ ልበል ፡ ላመስግነው
ኃይልና ፡ ጥበብም ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ሃሴት ፡ ታደርጋለች ፡ ዘወትር ፡ ነፍሴ
ሁሌ ፡ እያቀረበች ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ክብር ፡ ለሚገባው ፡ ክብር ፡ ይሁን
በዙፋኑ ፡ ላለው ፡ ኦ ፡ ልዘምር
ለአማልክት ፡ አምላክ ፡ ይሁን ፡ ስግደት
በሠማይ ፡ በምድር ፡ ኃይልና ፡ በረከት
ሃሌሉያ ፡ ልበል ፡ ላመስግነው
ኃይልና ፡ ጥበብም ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ሃሴት ፡ ታደርጋለች ፡ ዘወትር ፡ ነፍሴ
ሁሌ ፡ እያቀረበች ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ክብር ፡ ለሚገባው ፡ ክብር ፡ ይሁን
በዙፋኑ ፡ ላለው ፡ ኦ ፡ ልዘምር
ለአማልክት ፡ አምላክ ፡ ይሁን ፡ ስግደት
በሠማይ ፡ በምድር ፡ ኃይልና ፡ በረከት
"አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ይሁንለት
አምልኮ ፡ ስግደት ፡ ይሁንለት
ለንጉሡ ፡ ለንጉሡ"
|