Daniel Amdemichael/Yesew Ej Yelielebet/Bersu Lay

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን በእርሱ ላይ ጣልኩና

ዝማሬን ዘመርኩኝ በገና ያዝኩና

አንተ አምላክ ነህ ብዬ የልቤን ብነግረው

እግዚአብሔር መንገዴን መልካም አደረገው (፪x)


ማነው ተጨንቆ ሽቅብ ያደገ

የእራሱን ጸጉር ነጭ ያደረገ

ዛሬ በሆነው ነፍሴ አመስግኜው

ነገን አላውቅም ነገ የእርሱ ነው

የዘለዓለሙ ጌታ ለዘለዓለም ያዳነኝ

በዚህም በምድር ላይ እንዲያውቃል እንዲያኖረኝ


አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን በእርሱ ላይ ጣልኩና

ዝማሬን ዘመርኩኝ በገና ያዝኩና

አንተ አምላክ ነህ ብዬ የልቤን ብነግረው

እግዚአብሔር መንገዴን መልካም አደረገው (፪x)


ምግብን ከሰጠ ለሠማይ ወፎች

አምላክ ካሰበ ለምድር አበቦች

ለሰራኝማ ፈጥሮ በአምሳሉ

ተአምራት አለው ልቁም በቃሉ

ሃሳቤን በእርሱ ጥዬ እምነቴን ላጠንክረው

በኢየሱስ በጌታዬ ልቤን ላሳርፈው


አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን በእርሱ ላይ ጣልኩና

ዝማሬን ዘመርኩኝ በገና ያዝኩና

አንተ አምላክ ነህ ብዬ የልቤን ብነግረው

እግዚአብሔር መንገዴን መልካም አደረገው (፪x)


እርሱ ስለእኔ ያስባል ያለ

በጌታ ታምኖ ሸክሙን የጣለ

ማይነቃነቅ መሰረት ያለው

የጊዜው ወጀብ ያላናወጠው

ተመስገን ንገሥ ይላል በኢየሱስ ልቡ ያረፈ

ሁልጊዜ በአምላኩ ላይ እየተደገፈ


አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን በእርሱ ላይ ጣልኩና

ዝማሬን ዘመርኩኝ በገና ያዝኩና

አንተ አምላክ ነህ ብዬ የልቤን ብነግረው

እግዚአብሔር መንገዴን መልካም አደረገው (፪x)