በአምላኬ (Beamlakie) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 6.jpg


(6)

የሰው ፡ እጅ ፡ የሌለበት
(Yesew Ej Yelielebet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝበአምላኬ ፡ በስራው ፡ ከምደነቅ ፡ በቀር
በቂ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ ዘርዝሬ ፡ እንዳልናገር (፪x)
ሺህ ፡ ቃላት ፡ ደርድሬ ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ባወራው
የአምላኬ ፡ ቸርነት ፡ ከዚያም ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ ነው
ዝም ፡ ብዬ ፡ ሁሌ ፡ አመሰግናለሁ
እርሱ ፡ በሰጠኝ ፡ ፀጋ ፡ መልሼ ፡ አከብረዋለሁ

ለአምላኬ ፡ ምሥጋናው ፡ ብዙ ፡ ነው
በደስታ ፡ ቆሜ ፡ ላመስግነው
የዕልልታው ፡ ድምጽ ፡ በቤቱ ፡ ይሰማ
ውዳሴ ፡ ለሆነው ፡ ገናና ፡ ክብርም ፡ ለእርሱ ፡ ነውና

ይደርደር ፡ በገናው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው ፡ ይሰማ
የጌታን ፡ ክብር ፡ ላወራ ፡ ቆሜያለሁ ፡ እኔማ
በጐነቱን ፡ እንድናገር ፡ አምላኬ ፡ መርጦኛል
ለእርሱ ፡ መለየቴን ፡ ሳስብ ፡ ምሥጋና ፡ ሞልቶኛል

ምህረቱ ፡ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
ይቅርታው ፡ ነው ፡ ወደር ፡ የሌለው
ያመልካል ፡ ብዙ ፡ የተተወለት
ይወዳል ፡ ምህረት ፡ የበዛለት
አምላክ ፡ ድንቅ ፡ ያደረገለት

ይሰበር ፡ ሽቶ ፡ ብልቃጡ ፡ መዓዛው ፡ ያወደው
ከእግሮቹ ፡ ስር ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ጌታዬን ፡ ላምልከው
ግድ ፡ የለም ፡ ዙሪያ ፡ ገባዪ ፡ በእኔ ፡ ግር ፡ ቢለው
ምን ፡ ያህል ፡ እንደወደደኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው

አዝበአምላኬ/በጌታዬ ፡ በስራው ፡ ከምደነቅ ፡ በቀር
በቂ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ ዘርዝሬ ፡ እንዳልናገር (፪x)
ሺህ ፡ ቃላት ፡ ደርድሬ ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ባወራው
የአምላኬ ፡ ቸርነት ፡ ከዚያም ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ ነው
ዝም ፡ ብዬ ፡ ሁሌ ፡ አመሰግናለሁ
እርሱ ፡ በሰጠኝ ፡ ፀጋ ፡ መልሼ ፡ አከብረዋለሁ

በፍቅሩ ፡ እጆቼን ፡ ይዞኛል
አይደክምም ፡ ሁሌ ፡ ይታገሰኛል
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ልበለው
መድሃኒት ፡ ለነፍሴ ፡ ፈውስ ፡ ነው
ክብር ፡ ታማኝ ፡ ለሆነው

ይክበር ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
ውዳሴ ፡ በሠማይ ፡ በምድር ፡ በታላቅ ፡ ዕልልታ
እስትንፋስ ፡ ያለው ፡ ይዘምር ፡ ይውጣ ፡ ምሥጋናዉ
በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ በላይ ፡ ከብሮ ፡ ጌታ ፡ ለሆነው