አመሰግናለሁ (Amesegenalehu) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 6.jpg


(6)

የሰው ፡ እጅ ፡ የሌለበት
(Yesew Ej Yelielebet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

 
አመሰግናለሁ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ንጉሥ ፡ ነውና
ሁሉን ፡ ይሁን ፡ ያለ ፡ ውብ ፡ አሮጐ ፡ የሰራው ፡ እርሱ ፡ ነውና
ብቻውን ፡ የሚኖር ፡ በታላቅ ፡ ብርሃን ፡ ሰው ፡ በማይቀርበው
የፍጥረት ፡ መሰረት ፡ ተቆጣጣሪ ፡ ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው (፪x)

ላመስግነው ፡ ቆሜ ፡ እንደገና ፡ ጥበብ ፡ ኃይልም ፡ የእርሱ ፡ ነውና
ከንፈሮቼ ፡ ለእርሱ ፡ ይዘምሩ ፡ እስትንፋሴም ፡ ይሁን ፡ ለክብሩ (፪x)

የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ ምህረቱ ፡ ከቦኝ ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ ላይ ፡ መቆሜ ፡ አሄ
ትንፋሼን ፡ መንገዴን ፡ በእጆቹ ፡ የያዘው ፡ ሆኖልኝ ፡ አቅሜ ፡ ሄሄ
ወራት ፡ ተቆጠሩ ፡ አመታት ፡ አለፉ ፡ ዛሬም ፡ ዘምራለሁ ፡ አሄ
በሕይወት ፡ እንድኖር ፡ ስለፈቀደልኝ ፡ አመሰግናለሁ ፡ ሆሆ

አቤት ፡ አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረት
አቆመኝ ፡ እኔም ፡ ልስገድለት
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አምላኬ ፡ ወዶኛል ፡ ጌታ ፡ ራርቶልኛል
ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፬x)

አመጸኛው ፡ ጠላት ፡ ከሚወረውረው ፡ ጦር ፡ እያስመለጠኝ ፡ አሄ
ቀስት ፡ እየሰበረ ፡ እሳት ፡ እያጠፋ ፡ በእጁ ፡ እየከለለኝ ፡ ሆሆ
ከአቻምናን ፡ አልፌ ፡ አምናንም ፡ አልፌ ፡ ኢኸው ፡ በሕይወት ፡ አለሁ ፡ አሄ
ቀሪውን ፡ ዘመኔን ፡ እንዲባርክልኝ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ ፡ ሆሆ

አቤት ፡ አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረት
አቆመኝ ፡ እኔም ፡ ልስገድለት
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አምላኬ ፡ ወዶኛል ፡ ጌታ ፡ ራርቶልኛል
ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፬x)

የእግዚአብሔር ፡ ደግነት ፡ በምን ፡ ይመዘናል ፡ መለኪያስ ፡ አለው ፡ ዎይ ፡ አሄ
ከጨለማው ፡ ዓለም ፡ አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጥቶ ፡ ታድጐኝ ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ ሆሆ
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የነፍሴ ፡ መድሃኒት ፡ የዓለሙ ፡ ቤዛ ፡ አሄ
በእርሱ ፡ ተመርጬ ፡ በደሙ ፡ ነጽቼ ፡ ቀረልኝ ፡ አበሳ ፡ ሆሆ

አቤት ፡ አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረት
አቆመኝ ፡ እኔም ፡ ልስገድለት
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አምላኬ ፡ ወዶኛል ፡ ጌታ ፡ ራርቶልኛል
ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ሳመልከው ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፬x)

"እንግዲስ ፡ እርምጃዬ ፡ የማስተዋል ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ የሚከብርበት
የምድር ፡ ላይ ፡ ኑሮዬን ፡ በትዕግሥት ፡ ሮጬ ፡ የምጨርስበት
በቀንም ፡ በማታም ፡ አምላኬን ፡ የመፍራት ፡ ጥበብ ፡ ይሁንልኝ
የሮጥኩት ፡ ሩጫ ፡ በእሳት ፡ ስፈተን ፡ አይቃጠልብኝ
ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ በዐይኔ ፡ እስካየው ፡ ድረስ ፡ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ልገዛ ፡ በውነት ፡ ልስገድለት
ውዱ ፡ ጌታ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ (፪x)
ከፍ ፡ ይበል ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ይንገሥ"