Daniel Amdemichael/Yesew Ej Yelielebet/Alresawem

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ርዕስ አልረሳውም ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል አልበም የሰው እጅ የሌለበት

ጌታ በሕይወቴ ወዶ ያደረገውን መቼም አልረሳውም እርሱ በሕይወቴ ፈቅዶ ያደረገውን መቼም አልረሳውም አልረሳውም ያደረገልኝን አልረሳውም ለእኔ የሆነልኝን አልረሳውም የአምላኬን ውለታ ዘወትር ልቀኝ ለሚያኖረኝ በደስታ

ሰው ሳያውቀኝ ቀድሞ ያወቀኝ አትፍራ ልጄ የእኔ ነህ ያለኝ ውስጤን ልቤን የጣልኩበት እግዚአብሔር ነው ያኔ በመከራ የደገፈኝ ሳለቅስ እምባዬን ያበሰልኝ የቅኖች አምላክ እግዚአብሔር አባቴ ነው (፪x)

ይሁን ያለው ሁሉ ይሆናል ሃሳቡን ማን ይከለክላል እንዴት ልርሳ መልካምነቱን ልዘምር እንጂ ምህረቱን

ተስፋ ላጣ ተስፋ ነው ለምስኪኑ ወዳጅ ላጣ ብቸኛ ነው ወገኑ ላመስግነው እንጂ እኔ ልወድሰው ኃይሌ ክብሬ ታሪኬም ኢየሱስ ነው

ሰው ሳያውቀኝ ቀድሞ ያወቀኝ አትፍራ ልጄ የእኔ ነህ ያለኝ ውስጤን ልቤን የጣልኩበት እግዚአብሔር ነው ያኔ በመከራ የደገፈኝ ሳለቅስ እምባዬን ያበሰልኝ የቅኖች አምላክ እግዚአብሔር አባቴ ነው

ዮሴፍን ከእስር ቤት ያወጣ ለሹመት ሽልማት ያበቃ የዳንኤል አምላክ ተዐምረኛ ከአንበሶኝ የሚያድን ከበላተኛ

አይገርምም ወይ ይሞታል የተባለው ሕይወት ዘርቶ በግሩ ቆሞ አየነው የቀመሰ ያውቀዋል የእርሱን ማዳን የተነካ በእግዚአብሔር ብርሃን

ጌታ በሕይወቴ ወዶ ያደረገውን መጄም አልረሳውም። እርሱ በህይወቴ ፈቅዶ ያደረገውን መቼም አልረሳውም አልረሳውም ያደረገልኝ አልረሳውም ለእኔ የሆነልኝን አልረሳውም የአምላኬን ውለታ ዘወትር ልቀኝ ለሚያኖረኝ በደስት። አዝ