ዓለም ፡ አታላይ (Alem Atalay) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 6.jpg


(6)

የሰው ፡ እጅ ፡ የሌለበት
(Yesew Ej Yelielebet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

 
ዓለሙም ፡ ምኞቱም ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ጠፊ ፡ ነው (፪x)
ዘለዓለም ፡ የሚያኖር ፡ የጌታን ፡ ፍቃዱን ፡ ማድረግ ፡ ነው (፪x)
አትታለል ፡ ልቤ ፡ በሚያብለጨልጨው
ከክፋቱ/ከአመጹ ፡ ጋራ ፡ ይህ ፡ ዓለም ፡ ጠፊ ፡ ነው
(፪x)

አዝዓለም ፡ ዓለም ፡ አታልይ ፡ ናት (፪x)
እውነት ፡ ሕይወትና ፡ መንገድ ፡ ጌታ ፡ ኦ ፡ ለታመኑበት (፪x)

ከእሳት ፡ ተጠብቆ ፡ ለሚቆየው ፡ ዓለም (፪x)
ነፍሴ ፡ አትጓጊለት ፡ በፍፁም ፡ ይቅርብሽ ፡ ግድየለም (፪x)
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ብቻ
ከእሳት ፡ ከጨለማው ፡ በእምነት ፡ ማምለጫ
(፪x)

አዝዓለም ፡ ዓለም ፡ አታልይ ፡ ናት (፪x)
እውነት ፡ ሕይወትና ፡ መንገድ ፡ ጌታ ፡ ኦ ፡ ለታመኑበት (፪x)

ሕይወትና ፡ ተስፋ ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ (፪x)
በእውነት ፡ ለታመኑበት ፡ የሚሰጥ ፡ ከጌታ (፪x)
ይህን ፡ ያስተዋለ ፡ ጌታን ፡ ሙጥኝ ፡ ይላል
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ እድፈት ፡ እራሱን ፡ ያነጿል
(፪x)

ዓለምን ፡ አትርፎ ፡ ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ቢያጐድላት
ከቶ ፡ ምን ፡ ሊጠቅመው ፡ ሁሌ ፡ ላይኖርባት
ብልጭልጯን ፡ ንቆ ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ የኖረ
እርሱ ፡ ነው ፡ ጠቢብ ፡ ሰው ፡ ያ ፡ ነው ፡ የተማረ