Daniel Amdemichael/Yehonal/Sinega

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሲነጋም ሲመሽም ሁልጊዜ የማስታውሰው ከልቤ የማይጠፋው ዘላለማዊው ፍቅርህ ነው (፪x)

እንዴት ይረሳል ያደረግህልኝ? በቀራንዮ የከፈልክልኝ ፍቅርህ በሕይወቴ ዛሬም ትኩስ ነው ግን ቃል አጠረኝ እንዳልተርከው

ብዘምር ቃላቶች ያጥሩኛል ብናገር ቃላቶች ያጥሩኛል ለፍቅርህ ምን ምላሽ ይገኛል ኦሆሆ

ሲነጋም ሲመሽም ሁልጊዜ የማስታውሰው ከልቤ የማይጠፋው ዘላለማዊው ፍቅርህ ነው (፪x)

አይታክተኝም ለሃገር ባወራ ስለ አንተ ክብር ስለ አንተ ዝና ምነው በሆነ ልቤ እንደ ጅረት እንደ ውኃ ፈሳሽ እንደ ገነት ምንጭ

አምልኮ ማደሪያህን ይሙላው ዝማሬ ማደሪያህን ይሙላው ዕልልታ ማደሪያህን ይሙላው ኦሆሆ (፪x)