Daniel Amdemichael/Yehonal/Meheret Yebezalet

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search


ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል
ርዕስ ምህረት የበዛለት
አልበም ይሆናል

አዝ
አቤት ምሕረት የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፪x)
አቤት ፀጋ የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፫x)
ያመስግን እንጂ ኦሆ
ስላደረግህለት ሌላ ምን ቃል አለው (፪x)
ሁሌ በልቤ እኔ የምመኘው
አንተን ማመስገን ሥምህን ማክበር ነው
ዓይኔ በርቶልኝ የውስጥ ሃሳቤ
ክብርህን አይቼ ልኑር ጠግቤ (፪x)

አንደበት ያለው ሁሉ ክቡር ሥምህን ከፍ ያድርገው ያመስግነው
ምሕረት ፀጋ የበዛለት ማዳንህን ይናገረው(፪x)
ከአማልክት መሃል አንተ ብቻህን ጌታ ነህ
አንተ ብቻህን አምላክ ነህ

አዝ
አቤት ምሕረት የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፪x)
አቤት ፀጋ የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፫x)
ያመስግን እንጂ ኦሆ
ስላደረግህለት ሌላ ምን ቃል አለው (፪x)
ሁሌ በልቤ እኔ የምመኘው
አንተን ማመስገን ሥምህን ማክበር ነው
ዓይኔ በርቶልኝ የውስጥ ሃሳቤ
ክብርህን አይቼ ልኑር ጠግቤ (፪x)

አቤቱ ጌታ አምላክ ሆይ
ወደ አንተ እገሰግሳለሁ (፪x)
ክብርህን ኃይልህን አይ ዘንድ
ይሄ ለእኔ ጥማቴ ነው (፪x)

ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው
ልበል ሥምህን ላክብረው
የአንተ መክበር ለእኔ ደስታ ነው

አዝ
አቤት ምሕረት የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፪x)
አቤት ፀጋ የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፫x)
ያመስግን እንጂ ኦሆ
ስላደረግህለት ሌላ ምን ቃል አለው (፪x)
ሁሌ በልቤ እኔ የምመኘው
አንተን ማመስገን ሥምህን ማክበር ነው
ዓይኔ በርቶልኝ የውስጥ ሃሳቤ
ክብርህን አይቼ ልኑር ጠግቤ (፪x)